Saturday, September 10, 2016

                        ዕንቁጣጣሽ

    ዕንቁጣጣሽ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የደስታ፣የብሩህ ተስፋና የአዲስነት ስሜት የሚያሳድር ነው፡፡ዕንቁጣጣሽየሚለው ስያሜ በቃል የተነገረ እንጂ በጽሑፍ የሠፈረ አልተገኘም፡፡ ኖም በቃል ትውፊት ሲነገር እንደ መጣ ...

      *ዕንቁ ብሎ አዕናቁ ከግእዝ የተወረሰ ቃል ነው፡፡ ዕንቁ ለአንድ፤ አዕናቁ ለብዙ ይነገራል፡፡ ጣጣሽ፡- “ፃዕ ፃዕከሚለው የግእዙ ቃል የተወረሰ ነው በአማርኛ ጣጣ፣ መባዕ፣ ግብር፣ መፍቀድ፣ ገጸ በረከት /በረከተ ገጽ/ ማለት ይሆናል፡፡ መጽሓፍተ ብሉያት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርበውን መባዕ፣ የሚገባውን ግብርፃዕፃዕይሉታል፡፡ በየዓመቱ ዕንቁጣጣሽ ማለታችን ‹‹ የዕንቁጣጣሽ ግብር፣ የእንቀጣጣሽ ገጸ በረከት ነው ›› ብለን የምሥራች ማሰማታችን ነው፡፡
በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዕንቁጣጣሽ የተበረከተው ለቀዳማዊ ምንይልክ /ምኒልክ/ እናት ለንግሥት ማክዳ ነው፡፡ ንግሥት ማክዳ ቀዳማዊ ምንይልክን /ምኒልክን/ በወለደች ጊዜ ሕዝቡ ንጉሥ ተወለደ ብሎ እልል እያለ ገጸ በረከት አቅርበዋልየአበባ ዕንቁጣጣሽ መባሉም መጀመሪያ ለንግሥቲቱ ስለ ተገበረ ነው፡፡ ለንጉሥ ቢሆን ኖሮ ‹‹ዕንቁ ፃዕፃሁ›› ይባል ነበር እንጂ ‹‹ዕንቁጣጣሽ›› አይባልም ነበር፡፡ በሸዋም ሕዝቡ ግብር አለብኝ ሲል ‹‹ጣጣ አለብኝ ›› ይላል፡፡

     *የዕንቁጣጣሽ ታሪክ ንግሥተ ሳባ የሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስትደነቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎቿ ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኙ በኢየሩሳሌም የማይገኙ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው ርሱም አንድ ነገር ሳይሰውር ገለጠላት ቤተመንግሥቱንና በቤተመንግሥቱ የሚገኙትን እጅግ በጣም የከበዱ እቃዎችን ሁሉ አስጎብኝቷት ሲያበቃ "ዕንቁጣጣሽ" (‹‹ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንሽ››) ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት /ሰጣት/ ይህም የተፈጸመው /ንግሥተ ሳባ ከንጉሥ ሰሎሞን ጋር የተገናኘችው/ በመስከረም ወር ነው ዕንቁጣጣሽ በዚህ ምክንያት ተጀምሯል፡፡
    *  ዕንቁጣጣሽ ግጫ ማለት ነው፤ ግጫ ደግሞ የሳር ዓይነት ነው፡፡ በመስከረም ወር ምድር በአዝርዕትና በአትክልት በአበባና በፍሬ የምትሸፈንበት በተለያዩ አበቦች የምታሸበርቅበት በመሆኑ ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ወሩን መሠረት ያደረገ ነው፡፡
=> ‹‹ዕንቁ›› እና ‹‹ጣጣሽ›› የሚባሉት ሁለት ቃላት ለይቶ መመልከት ይቻላል፡፡ ዕንቁ የሚባለው የከበረና ከማድናት በላይ የሆነ የጌጥ ዕቃ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ጣጣሽ ሲባል ደግሞ ‹‹ያንቺ ግዳጅ ዕንቁ ነው›› ማለት በዕንቁ ታጌጫለሽ፣ ታሸበርቂያለሽ፣ ከወራት ሁሉ የተለየሽ ነሽ ለማለት ወርኃ መስከረምን የሚገልጥ ነው፡፡    
   ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በእጣ ሲያካፍላቸው አፍሪካ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪካ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኀ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡
  1ነገ.101-10 ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሣባ / አዜብ የንጉሡን ጥበብ ከመስማት ማየትን መርጣ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ከብዙ ሠራዊቶቿ ጋር የእጅ መንሻ በመያዝ ሄደች፡፡ ንጉሡም በደስታ ተቀብሎ እርሱምእንቁ ለጣትሽ
ጌጥ ይሁንሽበማለት አራት አይነት ቀለም የሚታይበት በቀንና በሌሊት የምታበራ ቀለበት ሰጥቷታል፡፡ ወሩም ወርኀ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ወጥቷል፡፡

=> በተጨማሪም ይህ ወር የአበባ የርጥበት ስጦታ የሚሰጣጡበት ወር በመሆኑ ነው፡፡ የአበባ የርጥበት ስጦታ መስጠት የተጀመረው በኖኅ ዘመን ነው፡፡ ኖኅ የጥፋት ውኃ በጎደለ ጊዜ መጉደሉን ለማረጋገጥ ርግብን ልኳት የወይራ ቅጠል አምጥታለታለች፡፡ እርሱም የመርከቡን ጣራ አንስቶ ከወጣ በኋላ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት በማቅረብ ልዩ ልዩ ጸአዳ ሽታ ያላቸውንም አበቦችንም አቅርቧል ይህም በወርኃ መስከረም ነው፡፡ ኋላም ንግሥተ ሳባ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ዘንድ ስትሄድ 500 /አምስት መቶ/ ደናግልት ተከትለዋት ነበር የእልፍኝ አሽከሮቿም እነርሱ ነበሩ በዚያም ለንግሥታቸው አበባ ሰጥተዋታል የአበባውም /የእንቁጣጣሹም/ ስጦታ በእነርሱ ተፈጽሟል፡፡ ዛሬም ልጅ አገረዶች አበባ ቀጥፈው እንግጫ ነቅለው ሸልመው የሚያቀርቡበት ከሽማግሌዎችም ምርቃትን የሚያገኘበት ወር በመሆኑ ነው፡፡

  ዘመን መለወጫ
ዘመን መለወጫ መስከረም ወር የሆነበት ምክንያትብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ቢቆጥሩ 364 ቀናት ይሆናል፡፡
• “ሌሊቱም ከቀኑ ጋራ ይተካከላል፡፡ ዓመቱም ጠንቅቆ ቢቆጥሩት ሦስት መቶ ስልሳ አራት ቀን ይሆናል፡፡ /ሄኖክ.2644/ “ዘመናችንን እንደ
ቀድሞ አድሱ” /.ኤር.521/ እንዲል፡፡ በዘመነ ኖኅ ዓለምን ንፍር ውኃ አጥለቅልቆት ከቆየ በኋላ
ዳግመኛ ውኃው የጎደለበት በመሆኑ /ኩፋሌ 71/
በመጀመሪያው ወር መባቻም ምድር ታየችእንዲል፡፡
 ቅዱስ ዮሐንስ
የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር አባቶች ወስነዋል፡፡ /ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1-3/ መጽሐፈ ስንክሳርየመስከረም ወር የተባረከ ነው፡፡ እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች
መጀመሪያ ነው፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጎደለ ይሄዳልእንዲል፡፡
በአጠቃላይ ዘመን መለወጫ ከላይ ባየናቸው የተለያየ ስያሜ ይጠራ እንጂ ዘመኑ አዲስ እየተባለ ቢጠራም አዲስ መሆን ያለበት ወርና ወቅቱ ብቻ ሳይሆን የእኛ የክርስቲያኖች ሥርዓት ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነታችሁን አታርክሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና እያለ
በመዋዕለ ሥጋዌው ያስተምር ነበር፡፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በኀጥያት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ፣ በቅዱስ ቊርባን፣ በመልካም ተግባር አዲስ ልናደርገው ይገባናል፡፡

                           መልካም አዲስ አመት

No comments:

Post a Comment