እንደምን ሰነበታችሁ ውድ ክርስቲያኖች? . . . እስቲ አንዲት ጥያቄ ልጠይቃችሁ?
ሞትን ታውቁታላችሁ?
እኔማ አሁን ባለፈው ዕለት እንዳጋጣሚ አገኘሁት እና እባክህ ቃለ መጠይቅ ላድርግህ ብዬ ብጠይቀው
አሻፈረኝ አለ፡፡ ብለው ብሰራው . . . ወይ ፍንክች!!! "ኧረ ባክህ እንደው
ለአጭር ሰዓት ላስቸግርህ?" እሱ መቼ ሰምቶኝ፡፡
በመጨረሻም "በዮሐንስ አፈወርቅ?" ብዬ ስለምነው "ያኔ አስራ ሁለት
አመት ገትሮ አቁሞኛል፡፡ አሁን ደግሞ ሃያ አራት ዓመት ያደርግብኝ እንደሆነ መከራ ታሳየኛለህ፡፡" አለና እሺ አለኝ፡፡
እኔም የነገረኝን በማስታወሻዬ ፃፍኩት፡፡ ይኸው አሁን በክፍል በክፍል እንደሚሆን እንደሚሆን አድርጌ ለእናንተ እንደሚከተለው አቀረብኩት
. . .
ጥያቄ፡- ስለትውልድህ እና እድገትህ ብታጫውተኝ?