ከአቤል ተስፋዬ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
…እንግዲህ (አብዝታችሁ)
ብታነቡ የጌታችን ተከታይ ሆናችኋል፡፡ እርሱም ያነባ (ያለቅስ) ነበርና፤ በአልአዛር (መቃብር ላይ)፤ በከተማይቱ (ኢየሩሳሌምን)
ላይ፤ ይሁዳም ባገኘው ጊዜ አብዝቶ አዝኖ ነበር፡፡ ብዙዎች ሲያዝን አይተውታል ነገር ግን ሲስቅም ሆነ ፈገግ ሲል ለቅጽበት ስንኳ
በየትኛውም ጊዜ ያየው አንዳችም የለም፤ ከወንጌላውያኑ የትኛቸውም ይህን እንዳደረገ አልገለጹም፡፡ (ቅ.) ጳውሎስንም እንዲሁ፤ እንዳለቀሰ፤
ለሶስት አመታት ቀን ከሌሊት (ያለመቋረጥ) እንዳነባ ራሱም ገልጿል፤ ሌሎችም ስለርሱ ይህን መስክረዋል፤ እንደሳቀ ግን እርሱም የትም
ቦታ ላይ አልጠቀሰም ከሌሎች ቅዱሳንም መካከል ይህን እንዳደረገ የተገለጸ ማንም የለም፤ ስለ ሳራ (የአብርሀም ሚስት) (እንደሳቀች)
ተጠቅሷል ይኸውም (በሦስቱ መላዕክት) በተገሰጸችበት ወቅት ነበር፤ እንዲሁም የኖኸ ልጅ በተመሳሳይ ስለመሳቁ ተጽፏል፤ ይህን ባደረገበት
ወቅት ግን (በአባቱ ተረግሟልና) ነጻነቱን በባርነት ለወጠ፡፡
እንዲህ የምላችሁ ሳቅ
(ጨዋታ) የተባለን ሁሉ ለመኮነን አይደለም፤ አእምሯችሁ በከንቱነት እንዳይጠመድ ለማቀብ ነው እንጂ፤ እስኪ ልጠይቃችሁ በምቾት የምትንደላቀቁና
በከንቱነት የተዘፈቃችሁ ሆናችሁ ሳለ በሚያስፈራው (የጌታችን) የፍርድ መንበር ፊት ቆማችሁ እዚህ (በምድር) ላይ ሳላችሁ ስለሰራችሁት
ነገር አንድ በአንድ አትጠየቁምን? በእርግጥ
እንጂ… ምክንያቱም አውቀን በድፍረት ስለሰራነውም ሆነ ከአቅማችን በላይ ሆኖብን ስለበደልነው በደል ምላሽ እንድንሰጥ እንጠየቃለንና… ‹‹ በሰዎች ፊት
የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ (በሰማዩ) አባቴ ፊት እክደዋለሁ›› ይላልና ጌታ፡፡ አለጥርጥር ማናችንም ጌታን ወደን አንክደውምና አውቀንና
ፈቅደን አናደርገውም፤ ነገር ግን ይህም ቢሆን ከቅጣት አያድነንምና ይህንንም አስመልክቶ መልስ መስጠት ይኖርብናል፤ አውቀን ስለሰራነው
ብቻ ሳይሆን ሳናውቅ የበደልነውም ጭምር ያስጠይቀናል፡፡ ‹‹ በራሴ አንዳች አላውቅም፤ ነገር ግን ይህ ምክንያት ሆኖኝ ከፍርድ አላመልጥም
(አልድንም)›› ይላልና 1 ቆሮ 4፡4 ፤ደግሞም በሌላ ስፍራ እንዲህ ይላል ‹‹ ለእግዚአብሔር
ቀናኢነት ያላቸው ናቸውና ይህን ቆጥሬላቸዋለሁ፤ ነገር ግን በእውቀት አይደለም›› ይሁን እንጂ ይህ በቂ ምክንያት ሆኖ አልተገኘም፡፡
ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈበት ወቅትም ደግሞ (ሐዋ. ቅ. ጳውሎስ) እንዲህ ብሏል ‹‹ እባቡ ሔዋንን በረቂቅ ተንኮሉ እንዳሳታት
ሁሉ በጌታችን ካለ ቅንነት አእምሯችሁን እንዳይበርዘው እፈራለሁ››