Showing posts with label ሃይማኖተ አበው. Show all posts
Showing posts with label ሃይማኖተ አበው. Show all posts

Friday, December 16, 2016

                               ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ



      አቡነ ዜና ማርቆስ አባታቸው ዮሐንስ እናታቸው ማርያም ዘመዳ /ዲቦራ/ ይባላሉ፡፡ አባታቸው ዮሐንስ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት የአቡነ ጸጋ ዘአብ ወንድም ናቸው፡፡ እናታቸው ደግሞ የአቡነ ቀውስጦስ እኅት ናቸው፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ብሥራት የተጸነሱ አባት ናቸው፡፡ እኚህ አባት በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው እቅፍ ወርደው እሰግድ ለአብ እሰግድ ለወልድ እሰግድ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ሦስት ጊዜ ሰግደዋል፡፡


የገና ዛፍ
የገና ዛፍ ከየት መጣ ከእፅዋት ሁሉ የጽድ ዛፍ ብቻስ
ለምን ሆነ ?
የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርሰረቶስ
የልደት በዓል ሲከበር ዘውትር እያየናቸው ካሉና የበዓሉ አንድ
አካል እየሆኑ ከመጡ ነገሮች መሀከል ዋነኛው የገና ዛፍ ነው።
ይህን የገና ዛፍ አብዛኞቻችን ዝም ብለን ከማድረግ ባለፈ መቼቱ
የት እንደሆነ ምን አይነት ምስጢር እንዳለው የምናውቅ
አይመስለኝም ነገር ግን የቤተክርስቲያን ታሪክ ወደኋላ መለስ
ብለን ስናይ ምንጩ ከወዴት እንደሆነ ይነግረናል የመጀመሪያዎቹ
ክርስቲያኖችና ሐዋርያት በነበሩበት ዘመን ራሳቸውን የእውቀት
ባለቤት አድርገው የሚቆጥሩ በክርስትና ላይ የመጀመሪያውን
የምንፍቅና ትምህርት ማንሳት የጀመሩ  ግኖስቲክስ የሚባሉ
ሃሳውያን ነበሩ የስማቸው ትርጉም በግሪክ ቋንቋ ጠቢባን
አዋቂወች ማለት ነው። መሪያቸው ስምኦን መሰሪ ይባላል ይህ
ሰው በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሐዋርያትን የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ
በገንዘብ እንዲሸጡለት ጠይቋቸው የነበረ ደፋር ሰው ነው።
ታዲያ እነዚህ እርሱ የሚመራቸው እራሳቸውን ጥበበኞች ብለው
የሚጠሩ መናፍቃን ከፍልስፍና ሃይማኖታቸው ብዙ
አስተምህሮዎች መካከል ዋነኛው ሁለት አምላኮች አሉ
ብለው የሚያምኑት ነገር ሲሆን እነዚህ አማልክት አንዱ ክፉ
አንደኛው ደግሞ ደግ ናቸው ይላሉ።መልካም የሆኑና ጥሩ ናቸው

Tuesday, April 12, 2016

ሚያዝያ 6 ቀን የቅዱስ አዳም እና የቅድስት ሔዋን ዓመታዊ የዕረፍት መታሰቢያ በዓላቸው ነው!!! በረከታቸው በኛ ላይ ይደርብንና እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ኑሮ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ከፈጠረለት በኋላ በስድስተኛው ቀን ዐርብ የመጀመርያውን ሰው አዳምን ፈጠረ። እግዚአብሔር ሲፈጥረውም በእራሱ መልክ እና ምሳሌ ፈጠረው፤ በምድር ላይ ለሚኖሩ ፍጥረታት ሁሉ ገዢ አደረገው። እግዚአብሔርም አዳም ብቻውን በመሆኑ ከጎኑ አጥንትን ወስዶ ሔዋንን ፈጠራት። በተፈጠሩበት ምድር አዳም አርባ ቀን ፣ ሔዋን ደግሞ ሰማንያ ቀን ከቆዩ በኋላ ወደ ኤዶም ገነት አስገባቸው። ይህን መሠረት አድርጋ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወንዶች በተወለዱ በአርባ ቀናቸው ፣ ሴቶች በተወለዱ በሰማንያ ቀናቸው ተጠምቀው የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ታደርጋለች። እግዚአብሔርም በገነት መካከል ያሉትን ፍሬዎች እንዲበሉ ፈቀደላቸው። ነገር ግን ዕፀ በለስ ተብላ የምትጠራውን ፍሬ እንዳይበሉ አዘዛቸው። ከዚህች ፍሬ ብትበሉ የሞት ሞትን ትሞታላችሁ ብሎ አስጠነቀቃቸው። አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ አክብረው ለ7 ዓመት ያህል ገነት ኖሩ። ሰይጣን ዲያብሎስ በእባብ በኩል የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንዲያፈርሱ ፈተና አመጣባቸው። ዲያብሎስ በእባብ አድሮ ወደ ሔዋን ቀርቦ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። እሷም ዕፀ በለስን ብትበሉ ትሞታላችሁ እንደተባሉ ነገረችው። እባብም ለሔዋን ሞትን አትሞቱም ከእርስዋ በበላችሁ ጊዜ እንደ እግዚአብሔር ትሆናላችሁ ብሎ በሀሰት አታለላት። ሔዋንም የእባብን ሽንገላ ሰምታ እውነት እንደ እግዚአብሔር የሚሆኑ መስሏት ለመብላት ወሰነች። ከፍሬውም ወሰደችና ከባልዋ ከአዳም ጋር አብረው በሉ። በበሉም ጊዜ ጸጋቸው ተገፈፈ፣ የክብር ልብሳቸውን አጡ፣ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ፤የበለስን ቅጠል ሰፍተው ለበሱ። የእግዚአብሔርን ሕግና ትእዛዝ ስናፈርስ ጸጋችን ይገፈፋል፤ እግዚአብሔርም ያዝንብናል። አዳምና ሔዋንም የእግዚአብሔርን ድምፅ ሲሰሙ ፈርተው በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። እግዚአብሔርም አዳምን ጠርቶ፦ ወዴት ነህ? አለው። እርሱም በገነት ድምፅህን ሰማሁ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፥ ተደበቅሁም አለው። እግዚአብሔርም ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በላህን? ሲለው አዳምም ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ አለው። እግዚአብሔርም ሁላቸውንም በጥፋታቸው ምክንያት ረገማቸው። እግዚአብሔርም እባቡን ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ፣ ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ ብሎ ረገመው። ሔዋንንም በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ በጭንቅ ትወልጃለሽ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል ብሎ ረገማት። አዳምንም እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በልተሃልና ወደ መጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና ብሎ ረገመው። እግዚአብሔርም በበደላቸው ምክንያት ከረገማቸው በኋላ ከ ገነት አስወጣቸው፥ አዳምም የተገኘባትን መሬት አርሶ መብላት ጀመረ። አዳምና ሔዋን ከገነት ከወጡ በኋላ እግዚአብሔርን ያህል ጌታ፣ ገነትን ያህል ቦታ በማጣታቸው በሰሩት ኃጢአት ተጸጽተው እግዚአብሔር እንዲምራቸው ሱባኤ (ጸሎት) ያዙ። እግዚአብሔር ጸሎታቸውን እና ልመናቸውን ተመልክቶ እንደሚምራቸው ቃል ኪዳን ገባላቸው። ቃል ኪዳኑም “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ከ5500 ዘመን በኋላ አድንሃለሁ” የሚለው ነበር። ቅዱስ አዳም ሚያዝያ 6 ቀን በ930 ዓመቱ ዕድሜ ጠግቦ አረፈና በቀራንዮ ተቀበረ። እግዚአብሔርም እንደተናገረ አልቀረም ከእናታችን ድንግል ማርያም ተወልዶ አዳምን ከእነ ልጅ ልጆቹ አዳነን። በአጠቃላይ ከአዳምና ሔዋን ታሪክ የምንማረው አታድርጉ የተባልነውን ነገር ማድረግ እንደለለብን ፤እሱን አልፈን ግን ብናደርግ እስከ ሞት ድረስ መከራ ሊያመጣብን እንደሚችል መረዳት አለብን። እግዚአብሔር ደግሞ የይቅርታና የምሕረት አምላክ እንደሆነ እንረዳለን። ስለዚህ ለእግዚአብሔር ሕግና ትእዛዝ መታዘዝ ይኖርብናል።

Monday, January 25, 2016

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

                                                 
    ቤተ ክርስቲያን ማለት ሕንፃው፣ የክርስቲያኖች አንድነት /ጉባኤ/ እና የምዕመኑ ሰውነት በመሆኑ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የምንለውም በእነዚህ በሦስቱ ላይ የተሠራውን ሥርዓት ነው። አንዳንዶቻችን ቤተ ክርስቲያንን ከራሳችን አርቀን ሌላ አካል አድርገን ስለምንመለከት ሥርዓቱ እኛን የሚመለከት አይመስለንም። ሥርዓቱ ግን የተሠራው ለሦስቱም የቤተ ክርስቲያን ትርጓሜዎች መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው።
  ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንጩ ወይንም መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የቅዱሳን አባቶቻችን ጉባኤያት ውሳኔ /ሲኖዶስ/ እና አባቶቻችን ሊቃውንት በተለያዩ ጊዜ ያደረጓቸው ጉባኤያት ውሳኔዎች ናቸው።

Wednesday, January 28, 2015

የእመቤታችን አስደናቂ ዕረፍት



ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
(ምንጭ፡ የቤልጂየም ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን መካነ ድር)
ስለ እመቤታችን ዕረፍትና ዕርገት ቊጥሩ72አርድዕት አንዱየሚኾነው ቅዱስኢቮዲየስ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ስለነበረ በጥር ፳፩ የኾነ የቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍትና በነሐሴ ፲፮የተከናወነ በዓለዕርገቷን በዐይኖቹ የተመለከተውንየቅድስት ድንግል ማርያም ኅልፈተ ሕይወትና ፍልሰትበሚል ርዕስ ጽፏል፤
http://fenoteabew.blogspot.com/
 
ድርሳን ዘደረሰ አባ ኢቮዲየስ ሊቀጳጳሳት ዘአንጾኪያ በእንተ ዕረፍታ ወፍልሰታ ለማርያም” Evodius of Rome, Homily on the Dormition The falling asleep of Mary “An instruction which our holy and in every wise honourable father Abba Evodius, the archbishop of the great city Rome, who was the second after Peter the apostle,…” (የእኛ ቅዱስ እና በማናቸውም ረገድ ብልኅ እና የተከበረ አባታችን፣ የታላቋ የሮም ከተማ ሊቀ ጳጳስ፣ ከሐዋርያው ጴጥሮስ በኋላ ኹለተኛው በኾነው የቀረበ መመሪያ፡፡ የኹላችንም እመቤት፣ እግዚአብሔርንየተሸከመች ቅድስት ማርያምን አስመልክቶ፤ በእግዚአብሔር ሰላም በግብጻውያን አቈጣጠር በ፳፩ኛው የጦቢ (ጥር) ወር ቅዱስ ሕይወቷን ያበቃችውን እመቤታችን አስመልክቶ የቀረበልን አስተምህሮ አሜን)፡፡



. “Now it came to pass at the hour of the light on the twenty-first of the month Tobi, …” (በጦቢ ወርበ፳፩ በብርሃን ሰዓት ላይ በነጋታው፣ እውነተኛው ቃልክርስቶስ በኪሩቤል ሠረገላው ላይ ተቀምጦ እልፍ አእላፋት የሚቈጠሩ መላእክት ተከትለውት፣ በዙሪያው የብርሃን ኀይሎች ከብበውት እናዳዊት በእሳት ሠረገላ ላይ ኾኖ ከፊቱ እየዘመረለት፣መንፈሳዊ በገናን እየተመታ ከፍ ባለ ድምፅ ለኀያሉ ጌታችን ክብርእንዘምርለት አለ፡፡ መድኀኒታችን በመኻከላችን ቆመ፣በሮቹ ተዘጉወደ ኹላችንም እጆቹን ዘረጋቸው፤ ብዙዎች ደቀ መዛሙርት በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፤ ሰላምለእናንተ ይኹንአለን፡፡ ኹላችንም በአንድ ላይ ተነሥተን እግሮቹ ሥርወድቀን የአምልኮት ምስጋናን አቀረብንለት፤ ርሱምበሰማያዊዉ በረከቱ ባረከን፡፡ መላእክቱም አሜንብለው መለሱ፤ ርሱም ወደ አባቴ ጴጥሮስ በመዞርበረከት ልሰጣችኊ በመኾኑ መሠዊያዉን ጠብቀውአለው፤በዛሬው ቀን ከእናንተ መኻከል ታላቅስጦታ ማግኘት አለብኝአለ፡፡ እኛግን በእግሮቹ ላይ ተደፍተን አመለክነው እኛምከእናንተ መኻከል በዛሬው ዕለት ታላቅ ስጦታ ለመውሰድ እፈልጋለኊ ስትልምን ማለትኽ ነውብለን አጥብቀን ለመንነው፡፡ መድኀኒታችንም ሲመልስልንከዓለም ኹሉአብልጬ የመረጥኋችኊ ክቡራን ኅዋሶቼ ይኽቺቀን የአባቴ ዳዊት ትንቢት የሚፈጸምባት ቀን ናት፣ ንግሥቷ በወርቅ በተንቆጠቆጠ አልባሷ አጊጣ እና አሸብርቃ በቀኜትቆማለች (መዝ፵፬፥፱)፡፡
ዛሬለዘጠኝ ወራትበምድር ላይመኖሪያዬ ኾናየቆየችውን ድንግል እናቴን የምቀበልበት እናከእኔ ጋርወደ ሰማያት ሰማያዊ ቦታዎች ይዤያት በመውሰድ ለመልካሙ አባቴበስጦታ የማስረክባት ቀን ነው፣ ዳዊትም እንኳንበኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፤ ባልንጀሮችዋንምወደ አንተያቀርባሉ” (መዝ፵፬፥፲፬) እንዳለ፤ ርሱም በመለኮታዊዉ እናግሩም ድምፁየኔ ውድእናት ሆይተነሥተሽ ወደእኔ ነዪ(መሓ ፪፥፲) የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ወደ እኔ ነዪ (መሓ፪፥፲፫) አላት፤ አንቺከቄዳር ልጆችም በላይ ውብ ቆንዦ ነሽ (መሓ ፩፥፭) አንቺየተመረጥሽ ጎጆሆይ የመልካማ ርግብ መኖርያ ነሽ፤አንቺ የተመረጥሽ የአትክልት ስፍራ ያለምንም ዘር እና የወንድ ሩካቤመልካሙን ፍሬያፈራሽ (መሓ፬፥፲፪)አንቺ የወርቅ መሶብ ሆይ መናው እውነተኛው መናእኔ እንኳን የተሰወርኹብሽ(ዘፀ ፲፮፥፴፫-፴፬) አንቺ ስዉር ቅርስ እውነተኛው ብርሃን የተሰወረብሽ እና ከአንቺም ውስጥ ወጥቶ በመገለጽ በሰውልጆች ላይየተትረፈረፈ ሀብትያስገኘላቸው፡፡ተነሥተሽ ወደእኔ ነዪየእኔ ውብርግብ ሆይ(መሓ ፮፥፱) የእኔ ቅድስት መርዐት (መሓ ፬፥፰) የእኔ ንጽሕት መስክ፣ ከእኔ ጋር ወደ አትክልት ስፍራው እወስድሻለኊ (መዝ ፸፩፥፮) ከርቤ እና ጣፋጭ ቅመማ ቅመሜን እደረድርልሻለኊ(መሓ ፬፥፲፬) ከበታችሽም እንድታርፊበትያማረውን ምንጣፍ አነጥፍልሻለኊ፤ማርያም እናቴሆይ አንቺየተባረክሽ ነሽወደ ምድርወልደሽ አምጥተሽኛልና፡፡

እኔኹሉን መጋቢየኾንኹትን ያጠቡጡቶሽን የተባረኩ ናቸው፡፡ እንዲኹም በከፍታ ቦታዎች ወደሚገኙ ሰማያዊ ስፍራዎች ወስጄሽ በአባቴ በመልካም ነገሮች እመግብሻለኊ፡፡ እስከዚያው በጉልበትሽ ላይያስቀመጥሺኝ ድንግል እናቴ ማርያም ሆይበኪሩቤል ሠረገላ ላይ በማኖር ከእኔና ከቸሩ አባቴ ጋር ወደ ሰማያት እወስድሻለኊ፡፡ በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉየእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይበወለድሽኝ ዕለትበከብቶች በረትከላም እናአህያ ጋርበአንድ ላይከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯) እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ኪሩቤልም በሰይፈ ነበልባላቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበትመሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደግብጽ ምድርእንደተሰደድሽው ኹሉ(ማቴ ፪፥፲፫-፲፰) መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ)፡፡



. “Now when we heard these things, as our Saviour was saying them to His virgin mother,…” (እነዚኽን ነገሮች ስንሰማ፣ መድኀኒታችን ለድንግል እናቱ እንደተናገረው፣ በሥጋሊወስዳት እንደፈለገ ኹላችንም ዐወቅን፡፡ ኹላችንም ፊታችንን አዙረን አምርረን አለቀስን፤ የኹላችንም እናትቅድስት ድንግል ማርያምም ከእኛ ጋር በአንድ ላይአለቀሰች፡፡ መድኀኒታችንም ለምን ታለቅሳላችኊ አለን? አባቴ ጴጥሮስምጌታዬ እና አምላኬ ሥርዓት አልበኞቹ አይሁድ አንተን በሰቀሉኽ ጊዜ በወደቀብን ከባድዐዘን የተነሣ ለጥቂት ቀናት አልቅሰን ነበር ግን በኋላ ላይ አንተ ከሞት በመነሣትኽ እጅግተደሰትን፤ አንተም ወደ እኛ ቀርበኸን በረከትኽን ለገስኸን፤ በሥጋ የአንተ እናትብትኾንም የኹላችንም እናት ለኾነችው ወደድንግል እናትኽ ማርያም አደራ ጣልኽብን፡፡ አኹን ግን ርሷን ከእኛ የምትወስድብን ከኾነየሚወድቅብንን ከባድዐዘን ለመቋቋም ስለማንችል ርሷን ከመውሰድኽ በፊት እኛኑ አስቀድመንአለው፡፡ መድኀኔ ዓለምምየእኔየተመረጥኽ ጴጥሮስና በእኔ የተመረጣችኊ ሐዋርያቶች ሆይ በሙሉ ትቼያችኊ (ተለይቼያችኊ) እንደማልቀር እና ተመልሼ እንደምመጣ አልነገርኋችኹምን? (ዮሐ ፲፬፥፩-) ስለዚኽ ለማርያም ሞት ፈጽሞ ማልቀስ አይገባችኹም፤ ወደ እናንተ በፍጥነት ሳትመለስ በጭራሽ አልተዋትም፡፡

እኔምራሴን ከእናንተ እንዳልሰወርኹትኹሉ ድንግል እናቴም ፈጽሞ ራሷን ከእናንተ አትሰውርም፡፡ ስለዚኽ ኹልጊዜም ወደእናንተ ስመጣድንግል እናቴን ከእኔ ጋር አብራ እንድትመጣ በማድረግ ነፍሳችኊ እንዲቀደስ አደርጋለኊአለ፡፡ እዚኽ ላይ አባቴ ጴጥሮስ እና የተቀሩት ደቀ መዛሙርት ለመድኀኒታችንአምላካችን እና ጌታችን ከነጭራሹ ፈጽሞ የሞትን ጽዋእንዳትጋፈጥ ማድረግስ አይቻልም ነበርን?” አሉት፤ መድኀኒታችንምየእኔ ቅዱሳን ሐዋርያቶች ሆይ ይኼ ንግግር ከእናንተ በመምጣቱ በጣም ድንቅ ነው አላቸው፡፡ በመዠመሪያ የተናገርኹት ቃል ሊታበል ይችላልን? አይችልም አባቴ ከልክሏልና፡፡ገና ከመዠመሪያውም ኹሉም ሥጋ የለበሰ ሰው ኹሉ ሞትን ማጣጣም ያስፈልጋቸዋል ብዬፍርድ ፈርጃለኊ (ዘፍ ፫፥፲፱)፡፡እኔም የሰዎች ኹሉ ጌታ የኾንኹት በለበስኹት ሥጋየተነሣ ሞትንቀምሼ የሞትን ሰቈቃ ያጠፋኊትአለ(ሮሜ ፭፥፲፯)፡፡ አባቴ ጴጥሮስም በዚኽ ጊዜ ላይ እንደገናከአንተ ጋርእንድነጋገር ፍቀድልኝአለው፡፡ ጌታምተነጋገርአለው፡፡ አባቴጴጥሮስምጌታዬለእኛ በማዘን እመቤታችን የምቾታችን (የሐሤታችን) ምንጭ በመኾኗ ለጥቂት ጊዜ በሕይወት እንድትቆይ አድርግልንአለው፡፡ መድኀኒታችንም ሲመልስለት እያንዳንዱ ሰውበዚኽች ምድርላይ የተቀመጠለት የቆይታ ጊዜ አለ፤ ጊዜው ሲደርስም ለአንዲት ሰዓትም እንኳን በተጨማሪ ለመቆየት አይቻለውም አለው፡፡ አኹንስለዚኽ ለእናቴ የተቀመጠላት ጊዜ ዛሬ ይፈጸማል፡፡ አኹንሰውነቷን አኑራእና ከእኔጋር በክብር ወደ ሰማያት መኼድይገባታልና፤ የሰማያትን ሥርዓት ተመልከቱ፣ አባቴየውድ ልጁመቅደስን፤ እኔንጨምሮ እየጠበቅናት ነውና፡፡ ወደ አባቴ ሳልወስዳት በፊትእራሴ እኔበቅዱስ መሥዋዕት ከርሷ ጋር እንባርካችኋለንናአለን)፡፡
. “The women therefore that went with her, even the virgins that followed her, turned their face away, and all wept bitterly…” (ከርሷጋር በአንድነት ይኼዱ የነበሩትም ሴቶችተከትለዋት የነበሩትም ደናግል ፊታቸውን አዙረው ኹሉም አምርረው በሲቃድምፅ አለቀሱ፤ ቅድስት ድንግል ማርያምም አብራቸው አለቀሰች፡፡ ቸሩመድኀኒታችንምማርያም ድንግል እናቴ ሆይ ስለምን ታለቅሺያለሽ? አላት፤ አኹን ልቅሶሽን በመተው ለዘላለም ነዋሪ ወደኾነው ደስታመኼድ አለብሽ አላት፤ ሐዘን እና ለቅሶሽን በመተው በሐሤት እና በደስታ ለዘላለሙ መኖርይገባሻል፤ የምድር ነገሮች በሙሉ ትተሽ የሰማያት የኾኑትን መውረስ ይገባሻልናድንግል ማርያምም ለመድኀኒታችንስትመልስለትጌታዬ፣ አምላኬ እና ልጄ እንዴት ዐላዝን እና በልቤስ አላለቅስ? በጣም ብዙ ጊዜያት በሰው ልጆች ሞት በጣም ብዙ ቅርፆች እናዳሉት፣ ሊወስዳቸው ከመጣ በኋላም አስፈሪ እና አሰቃቂ ነገርእንዳለው ሲነገር ሰምቻለኊ፤ እነዚኽ ነገሮች ከኾኑ፣ እንዴት አላለቅስ እንዴት ብዬስ አስፈሪውን ቅርፁን ልመልከተው?” አለች፤ ጌታችን ኢየሱስምውዷ እናቴ ማርያም ሆይ ሞትን ፈጽሞ እንዳትፈሪው፣ማንኛውንም የሞትኀይል ለማውደም የሚችለው ከአንቺ ጋርአይደለምን? አላት፤ ብዙ ቅርጽ ያለው ጣዕረ ሞትን የዓለም ኹሉሕይወት እስትንፋስ የያዘው ከአንቺ ጋርእያለ እንዴት ትፈሪዋለሽን?” አላት፤ ጌታምበራሱ ራርቶራሱን ወደድንግል እናቱአስጠግቶ እንባዎቿን ጠራርጎላት በመለኮታዊ ከናፍሮቹ ሳማት፡፡

ከዚያም ጌታ ኢየሱስ በመሠዊያዉ ላይ በመኾን ኹላችንንም ባረከን፣ የሰላም ሰላምታውን አቅርቦልን፣ አባቴን ጴጥሮስንፍጠን ወደ መሠዊያዉ ተመልከትና አባቴከሰማይ የላከልኝን ንጹሓት አልባሳትን አምጣልኝ ድንግል እናቴን ላልብሳት ምክንያቱም የርሷን ቅዱስሰውነት በምንም ዓይነት ከምድር የተገኘ ጨርቅ መሸፈን አይገባውምናአለ፡፡ከዚያምአባቴ ጴጥሮስ ያማረውን ውብ ሸማ፣ ንጹሕ፣ ቅዱስ፣ በጣም ውድ እና ጣፋጭ መዐዛ የሚረጨውን ይዞመጣ፤ እጅግደማቅ ብርሃን የሚለቀውን ያማረ ሸማ ስንመለከት ኹላችንም በጣም ተደነቅን፡፡መድኀኔ ዓለምም ያማረውን ሸማ ከአባቴ ጴጥሮስ ላይተቀብሎት በራሱመንገድ ዕጥፋቶቹን በመዘረጋጋት፤ድንግልእናቱን ጠርቷት፣ ተነሺ የእኔ ብራማ ርግብ ክንፎችሽ በወርቅ የተንቈጠቈጡት ወደ እኔ ነዪ አላት (መዝ ፰፯፥፲፫)፤የእኔ ንጽሕት እና እንከን የለሽ ጠቦት ወደ እኔ ነዪአላት(መዝ ፷፰፥፴፩):፡

. “And she arose, the queen of all women, Mary the Virgin, the mother of the King of kings, to go unto her beloved Son, our Lord Jesus Christ…” (የሴቶች ኹሉንግሥት፣ ድንግል ማርያም፣ የነገሥታት ንጉሥእናት ወደተወዳጁ ልጇወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመኼድ ተነሣች፡፡ ኹላችንም ከተቀመጥንበት ተነሥተን እጆቿን እና እግሮቿን እያነባን ሰላምታን ሰጠናቸው፤ ከዚያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውድልጇ ሰላምታ አቅርቦላትወደ ዘረጋኹልሽ አልባሳት ውስጥግቢ እናፊትሽን ወደምሥራቅ መልሺእና ጸሎትአቅርቢ፤ ከዚያበኋላ መጐናጸፊያው ላይ ጋደም በይ እና በምድር ላይ ለተወለዱ ሰዎች በሙሉ ጸሎትሽን አሟይአለ፤ የሴቶች ኹሉ ልዕልት፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የነገሥታት ኹሉ ንጉሥ እናት ከተቀመጠችበት ተነሥታ መድኀኒታችን በእጆቹ ወደዘረጋላት መሸፋፈኛ መኻከል ገባች፡፡ በቆመችበት ፊቷን ወደ ምሥራቅ አግጣጫ አዙራበሰማይ ነዋሪዎች ቋንቋ ጸሎቷን አቀረበች፡፡ ጸሎቷንም እንደጨረሰች አሜንአለች፤ እኛምኹላችንም ከተቀመጥንበት ተነሥተን አሜን ብለን መልስ ሰጠናት፡፡ ከዚኽ በኋላ በመሸፋፈኛ አልባሳቱ ላይ ጋደም ብላ እጆቿን ተደግፋ ወደ ምሥራቅ አግጣጫ ፊቷን አዞረች፡፡

ከዚያም መድኀኒታችን ከርሷ ጋር በቤተ መቅደስ ሲያገለግሉ ከነበሩትና መድኀኒታችንንእስከ እግረመስቀል ሲከተሉ ከነበሩ ደናግል ጋርበአንድ ላይእንድንጸልይ ለጸሎት እንድንቆም አደረገን፡፡ ክርስቶስ በተሰቀለበት ጊዜ ሴቶቹ ተከትለዋት መጥተው ነበር፡፡ እኛም በቤተ መቅደስ ለምንማገልገል እንዳቆሙ ስንጠይቃቸው? እነርሱም የእግዚአብሔር አብ ቃል ክርስቶስ በተሰቀለበት ቀንኹሉም ቦታዎች ሲለወጡ ተመልክተን ነበርአሉን፡፡ ፀሓይጨልማ ነበር፣ ጨረቃ ደም መስላ ነበር ከዋክብትም ከሰማያት ወደምድር ወድቀው ነበር፡፡ እኛም በጣም ፈርተን የቅዱሳን ኹሉ ቅዱስ ወደኾነው የጌታ ቤተ መቅደስ ውስጥሸሽተን ገባንበሩንም ጥርቅም አድርገን ዘጋነው፡፡ ወዲያውኑም ኀይለኛ መልአክ ከሰማይ በታላቅ ቁጣ በእጁ ውስት የሚያብለጨልጭሰይፍ ይዞወደ ምድርሲወርድ ተመለከትን፣ በያዘው ሰይፍም መጋረጃውን መኻል ለመኻል ከላይወደታች እኩልበእኩል ቀደደው (ማቴ ፳፯፥፶፩)፡፡ከዚያም ታላቅድምፅኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ ነቢያትን የምትገድል ወደርሷ የተላኩትንም የምትወግር ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታችእንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድኊ! አልወደዳችኹምም እነሆቤታችኊ የተፈታ ኾኖ ይቀርላችኋል” (ማቴ፳፫፥፴፯) የሚልሰማን እንደገና ስንመለከት ለመሠዊያው ተመድቦ የነበረው መልአክ በመሠዊያው በላይ ሰይፉን ይዞበታላቅ ቁጣሲበርር ተመለከትን፤ እነዚኽ ነገሮች በሙሉሲኾኑ ባየንጊዜ፣ ጌታበሰዎቹ በጣምእንደተቆጣና በርግማን ሥር እንዳንወድቅ በማሰብ ከእኛ ጋር ወደነበረችው እናቱም በፍጥነት እንደመጣን ዐወቅን፣ ይኽነንም መጋረጃውን ከቀደደው የጌታመልአክ አፍሰማንአሉ(ማቴ ፳፯፥፶፩)፡፡



፲፩. “The twelve virgin s therefore and all the women also who were with us, were all weeping with us together,…” (ዐሥራኹለቱ ደናግል እና ከእኛ ጋር የነበሩት ሴቶችበሙሉ ድንግል ማርያምን በዙርያዋ ከብበን የተማርነውን የሰማያዊ ምስጋና መዝሙር ስንዘምር ቆመንስናለቅስ ነበር፡፡ ክርስቶስም ለእናቱ ክብርእጆቹን በጉንጮቿ ላይ አድርጎ ከጐኗተቀምጦ ነበር፡፡ ለረዥም ጊዜ በዝማሬ ላይ ሳለን ክርስቶስ ለእናቱ ሰላምታ አቅርቦላት ወደውጭ ይዞንወጣ፡፡ ድንግልምኢየሱስ ሆይ እውነተኛው ያለምንም ነውርነቀፋ የወለድኹኽ ልጄ፣ የኀያሉ እግዚአብሔር ልጅ እና ውዱ ልጄ ልለምንኽ፣ የወለድኻትን እናትኽን እንዳትረሳት፣ጌታዬ ሆይ፣የሞት ጥላእንዳይቀርበኝ፤ ውዱልጄ ሆይየአምባገነኑ የሞትኀይሎች እናየድቅድቁ ጨለማሥልጣናት ይርቁዘንድ፡፡ የብርሃን መላእክት ይቅረቡኝ እንጂሞትን የማያውቁት ትሎች እንዳሉ ባሉበት ይኹኑ፡፡ የውጭው ጨለማብርሃን ይኹን፡፡ የሐሰት ከሳሾች አፍይዘጋ፡፡ በጥልቁ እንጦርጦስ የሚገኘው እሳትየሚተፋው ዘንዶወደ አንተስመጣ ሲመለከት አፉ የተዘጋ ይኹን፡፡ ውዱ ልጄ ሆይ የጥልቁ እንጦርጦስ አዛዦች ከእኔ እንዲሸሹ እና ነፍሴን እንዳያስፈራሯት እዘዛቸው፡፡ በእነዚኽ መንገዶች የሚገኙት አደናቃፊ ድንጋዮች ከፊቴይውደሙ፡፡ በመጥፎ ዐይኖቻቸው የሚያዩኝን በቀለኞችን ከልለኝ፡፡ ልክ እንደ ባሕር ማዕበል የሚናወጠው የሚንቀለቀለው የእሳት ወንዝ፣ ጻድቃን እና ኀጥኣንን ለኹለት የሚከፍለው በማልፍበት ጊዜነፍሴን ፈጽሞእንዳይነካት፤ ምንምኀፍረት በሌለበት ፊቴ አመልክኻለኹና ከዘመናት እስከ ዘመናት ኀይልእና ክብርየአንተ ናቸውአሜን)፡፡

፲፪. “And our Lord Jesus Christ said to His mother with His gentle voice, Be of good cheer, O Mary my mother…” (ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን ድንግል ማርያም ለስለስ ረጋ ባለ አስደሳች አንደበቱ ማርያም እናቴ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አላት፡፡ እነዚኽ ኹሉ ነገሮች በአንቺ ውስጥፈጽሞ ቦታስለሌላቸው ከአንቺ አርቄ አባርርልሻለኊ፤ በእነርሱ ፈንታ ለዘላለሙ ማረፊያሽ የኾኑትን የሰማያዊ ማረፊያ ቦታዎች እና በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም የሚገኙትን መልካሞች ነገሮችን አዘጋጅቼልሻለኊ፡፡ አካልሽ በውስጡ የሚሸፋፈንበት ከገነት የመጣውን ሰማያዊ መሸፈኛ እና እጅግ ያበቡትን የዘንባባ ዝንጣፊዎች አዘጋጅቼልሻለኊ፡፡ ቅዱስነፍስሽን ከእኔጋር ወደሰማይ በመውሰድ ለመልካሙ አባቴ በስጦታነት አበረክታታለኊ፣ እኔንየወለድሽኝ አንቺቅድስት ሆይከስጦታዎች ኹሉእጅጉን ከፍያልሽ ስጦታነሽናአላት፤ ጌታችን ሐዋርያቱንእኔየዓለም ሁሉሕይወት እስትንፋስ ባለኹበት ሞትን ማየት ስለማይገባት የውድእናቴ ነፍስመሰናበቻዋ ጊዜበመቃረቡ ለጥቂት ጊዜያት ወደ ውጭ እንውጣአላቸው፡፡ እነሆ አኹን እኛን በመጠበቅ በአንድ ላይ ኹሉም የሰማያት ኀይሎች ኹሉተሰብስበዋልና፤ ስለዚኽ ርሷ ጋደም ብላ እንዳለች ትተናት ጌታን ተከትለን ኹላችንም ወደ ውጭ ወጣን፤ ከርሷ ጋር የተሰበሰቡት ደናግል ዮሐና እና ሰሎሜ እንዲኹም ኹሉምታማኝ ሴቶችሊያገለግሏት በውስጥ ቀሩ፡፡ ጌታችን በመግቢያው በር ላይ በውጭ በሚገኝ አንድድንጋይ ላይተቀምጦ ሳለኹላችንም ከብበነው በዙሪያው ቆምን፡፡ ወደሰማይ ተመልክቶ በከፍተኛ ድምፅሞት ሆይ መኖሪያኽ በስተደቡብ በሚገኙት የማከማቻ ስፍራዎች የኾነው ድል ነሥቼኻለኊና ሥጋበለበሱ ፍጡራን ላይም በሙሉ ሥልጣን ሰጥቼኻለኊ እናወደ ድንግል እናቴ ና፣ ቅረባት ትመልከትኽ ግንማርያም እናቴምንም ልታይኽ እስከማትችልበትጊዜ ድረስማቃጠልኽ እናአሸናፊነትኽ ይውደም፡፡ ከዚያ በኋላ ግን (እናቴ ካረፈች በኋላ) ለዘላለሙ የምትለብሰውን አስፈሪ ቅርጽ እና ማቃጠልኽን እንዲኹም አሸናፊነት መልሰኽ ተጐናጸፍ፡፡ በአፍታ ቅጽበት እና በዐይን ብልጭታ ከሰውልጆች ኹሉስሙ እጅግአስፈሪ የኾነው ሞት ቀረበ፡፡ ልክበዐይኖቿ እንዳየች ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታ ልጇ ተቀምጦበት ወደነበረው ቦታ መጥታ በዕቅፉ ውስጥ ወደቀች፡፡ የእግዚአብሔር ቃልምበነበርንበት ቦታከመኻከላችን ተቀምጦ ሳለ ሰማይ እና ምድርን መላቸው፡፡ እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ የከበረ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው፣ ይኽም ለቅዱስ አካሏ ማኖሪያ ቦታ እስኪያዘጋጅ ድረስ ነበር፡፡ ኹሉም በዙሪያዋ ከበው የነበሩት ሴቶች ዕረፍቷን በተመለከቱ ጊዜእጅግ ዐዝነው አለቀሱ፡፡ ሰሎሜም ወደውጭ ወጥታበጌታዋ እግርላይ ተደፍታጌታዬ አምላኬ ተመልከት ውድ እናትኽ ዐርፋለችብላ አመለከችው፡፡ ዛሬታላቅ ዐዘንእና መነጠል የወደቀብን ለእኛ ወዮውልን፡፡ አንተ በአጠገቧ ብትኖር ኖሮአትሞትም ነበር፡፡ ጌታ ኢየሱስምእናቴድንግል ማርያም አትሞትም ይልቁንም ለዘላለም ትኖራለች፤ የእናቴ ሞትሳይኾን የዘላለም ሕይወት ነው እንጂአለ፡፡ ቅዱሱአመስጋኝ ዳዊትን በመንፈሳዊ በገናው ጮኾበመዘመርበጌታፊት የቅዱሳኑ ሞት እጅግ የከበረ ነው” (መዝ ፻፲፭፥፲፭) የነገሥታት ኹሉ ንጉሥ የኾነው የክርስቶስ እናትማርያም ደስይበልሽ፤ ይኽስለ እውነተኛዋ ንግሥት ማርያም የተናገርኩት ትንቢት የተፈጸመበት ቀንነው” (መዝ፵፬፥፱) በማለት ዘመረ)፡፡