Wednesday, September 23, 2015

ተቀጸል ጽጌ- የዐፄ መስቀል


 ተቀጸል ጽጌ ማለት የአበባ በዓል ማለት ነው፡፡ ክረምቱ፣ ድጡ፣ ማጡ፣ ችግሩና ጨለማው ተወግዶ ምድር በልምላሜ የምታሸበርቅበት፣ በአበባ የምትደምቅበት ወቅት በመሆኑተቀጸል ጽጌ እየተባለ ይከበራል፡፡የተቀጸል ጽጌ በዓል የተጀመረው በ6ኛው ምዕተ ዓመት በዐፄ ገብረ መስቀል አማካይነት ሲሆን በዓሉ የሚከበረው የክረምቱ ማብቃት የሚያበስሩ አበቦች በሚፈኩበት ወር በመስከረም 25 ቀን ለንጉሡ የአበባ ጉንጉን /አክሊል/ በማበርከት ነበር፡፡

አንድም የዐፄ መስቀል በመባል ይታወቃል፡፡ መስቀሉ ለብዙ ዘመን በእስክንደርያ ሲኖር በግብፅ ያሉ እስላሞች እየበዙ ኃላቸው እየጠነከረ ሲሔድ በእስክንድርያ በሚኖሩ ክርስቲያኖች ላይ ስቃ ያጸኑባቸው ጀመር፡፡ ክርስሰቲያኖቹም አንድ ሆነው ጸሎት እያደረጉ መከራው ሲጸናባቸው መክረው ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ንጉሥ ዐፄ ዳዊት መልእክት ላኩ፡፡€œንጉሥ ሆይ በዚህ በግብፅ ያሉ እስላሞች መመከራ አጽነተውብናልና አስታግስልን€ ብለው ጠየቁት፡፡ ዐፄ ዳዊትም ለመንፈሳዊ ሃይማኖት ቀንተው የክርስቶስ ፍቅር አስገድዷቸው 20,000 ሠራዊት አስከትለው ወደ ግብፅ ዘመቱ፡፡ በወቅቱ ነገወሦ የነበረው መርዋን እልጋዴን፣ ልጁ አሕመድ እንዲሁም በግብፅ ያሉ ኃያላን ፈሩ ተሸበሩ፡፡ ንጉሡ ዳግማዊ ዳዊትም እንዲህ የሚል መልእክት ለእስላሞቹ ላኩ፡፡¢€œበተፈጥሮ ወንድሞቻችሁ ከሆኑት ክርስቲያኖች ካልታረቃችሁ ሀገራቸችሁን መጥቼ አጠፋለሁ€ የሚል ማስጠንቀቂያ ላኩ፡፡ የንጉሡ መልእክትም ፤መርዋን እልጋዴንና እስላሞቹ እንደደረሳቸው ፈርተው እንደጥንቱ በሃይማኖታቸው ጸንተው በሰላ እንዲኖሩ ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር ታረቁ፡፡ መታረቃቸውን ዐፄ ዳዊት ሰሙ፡፡ በዚህም ጉዳይ ንጉሡ ደስ አላቸው፡፡

እግዚአብሔርንም አመሰገኑ በግብፅ የሚኖሩ ክርስቲያኖችም ከ12,000 ወቄት ወርቅ ጋር ደስታቸውን ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለዳግማዊ ዳዊት በደብዳቤ አድርገው ላኩላቸው፡፡ ንጉሡም የደስታውን ደብዳቤ ተመልክተው ደስ አላቸው ወርቁን ግን መልሰው በመላክ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጻፉ፡፡ በግፅ የምተኖሩ የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ የላካችሁልኝ 12,000 ወቄት ወርቅ መልሼ ልኬላችኋለሁ፡፡ የእኔ ዓላማ ወርቅ ፍለጋ አይደለምየክርስቶስ ፍቅር አስገድዶኝ በተቻለኝ ችግራችሁንሁሉ አስወገድሁላችሁ አሁንም የምለምናችሁ በሀገሬ ኢትዮጵያ ረሐብና ድርቅ ቸነፈር ስለወረደብኝ መድኃኒታን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀልና የቅዱሳን አጽም ከሌሎች ክቡራን ዕቃዎች ጋር እንድትልኩልኝ ነው የሚል ነበር፡፡

በእስክንድርያ ያሉ ምእመናን ይህ መልእክት እንደደረሳቸው ከሊቃነ ጳጳሳትና ከኤጲስ ቆጶሳቱ ጋር ውት በማድረግ ይህ ንጉሥ ታላቅ ክርስቲን ነው፣ ስለዚህ ልቡን ደስ እንዲለው የፈለገው የጌታችን ግማደ መስቀል፤ ከመስቀሉ ጋር ጌታ በዕለተ ዐርብ ለብሶት የነበረው ቀይ ልብስ ከለሜዳው፤ ሀሞት የጠጣበት ሰፍነግ/ጽዋ/፤ ዮሐንስ የሳለው ኩርዓተ ርዕሱስዕል እንዲሁም የቅዱሳን አፅም ጋር አሁን በመለሰው ወቄት ወርቅ የብርና የነሐስ የመዳብና የወርቅ ሳጥን አዘጋጅተን እንላክለት ብለው ተስማሙ፡፡ በክብርና በሥነ ሥርዓት በሠረገላና በግመል አስጭነው መስከረም 10 ቀን 1395 ዓ.ም ስናር ድረስ አምጥተው ባስረከቧቸው ጊዜ በእጃቸው እያጨበጨቡ በእግራቸው እያሽበሸቡ በግንባራቸው እየሰገዱ በክብር ተቀበሏቸው፡፡ መስከረመወ 10 ቀን በየዓመቱ ንጉሡ መስቀሉን የተረከቡበት ቀን ስለሆነ ዐፄ መስቀል፤ ተቀጸል ጽጌ እየተባለ ይከበራል፡፡

ይህ በዓል በየዓመቱ መስከረም 10 ቀን ዐፄ ዳዊት ከግብፃውያን ጳጳሳት እና ንጉሥ እጅ መስቀሉን የተረከቡበትን ቀን በማዘከር ከ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ መስቀሉን ወደ ኢትዮጵያ ካመጡበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ነገስታቱ ልብሰ መንግስታቸውን በመልበስ፤ ካህናቱ ጥንግ ድርብ ለብሰው ዝማሬ በማቅረብ፤ ምዕመናን ፀአዳ ለብሰውና አሸብርቀው በዓሉ ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ማብቂያ ድረስ ሲከበር ቆይቷል፡፡ዛሬም የአድባራት እና የገዳማት ሊቃውንት ልብሰ ተክህኖአቸውን ለብሰው የብር መቋሚያ እና ጸናጽል ይዘው ወደ መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በመሔድ ተቀጸል ጽጌ እያሉ እያሸበሸቡ በዓሉ ይከበራል፡፡

"ውእቱ ዝንቱ መስቀል ወቦቱ ንትመካህ ከመ ንሰብሖ እንሰግድለት ዘንድ የምናከብረው፣ እናከብረው ዘንድ የምንመካበት ይህ መስቀል ነው፡፡" /ጸሎተ ኪዳን/ እንደተባለው ሕይወትና ድኅነትን ያገኘንበት የሲኦልን እሳት ተሻግረን ወደ ገነት የገባንበት የአምልካችን ፍቅር የተገለጠበት ዐውድ በመሆኑ መስቀሉን እያሰብን በዓሉን እናከብራለን፡፡

No comments:

Post a Comment