ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃ እና መምህር ነበረ “ወሀሎ አሐዱ ብእሲ እምፈሪሳውያን ዘስሙ ኒቆዲሞስ መልአኮሙ ለአይሁድ”
ዮሐ3÷1 እንዲል፡፡ ሳምንቱ (ሰንበቱ) በእርሱ የተሰየመበት ዋናው ምክንያት ይህ ሰው በሌሊት እየመጣ ምስጢረ ጥምቀትን፣ ዳግም ልደትን ከጌታችን
ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ እግር ስር ቁጭ ብሎ የተማረበት ቀን መታሰቢያ ስለሆነ ነው፡፡ በዚህም ትምህርቱ ጌታችን ዋና የሆነውን
እና ሰው ከውሀ እና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንደማይገባ በግልጽ አስተምሮታል፡
ኒቆዲሞስ ከቀን ይልቅ በሌሊት መማርን ስለምን መረጠ?
ኒቆዲሞስ ይህንን ያደረገው ስለሶስት ነገር እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይናገራሉ ያስተምራሉ፡፡