ስያሜው የቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ በዚህ እለት የፈሪሳውያን
አለቃ ኒቆዲሞስ በሌሊት ወደ ጌታ መጥቶ ሲማር ጌታም ምስጢረ ጥምቀትን ዳግም ልደትን ለኒቆዲሞስ እንዳስተማረው እየጠቀሰ ቅዱስ ያሬድ
ዮሐ 3 ላይ ያለውን ወንጌል ስለዘመረው የእለቱ ስያሜ ኒቆዲሞስ ተብሏል፡፡
በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች
በገባሬ ሰናይ ዲያቆን ፡- ሮሜ 7፥ 1-19
በንፍቅ ዲያቆን፡- 1ዮሐ 4፥18-ፍጻሜ
በንፍቅ ቄስ ፡- የሐዋ 5፥ 34
ምስባክ፡-
ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፤
አመከርከነ ወኢተረክበ ዐመጻ በላዕሌየ፤
ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው፡፡
አማርኛ
፡-
ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ፤
ፈተንከኝ ምንም አላገኘህብኝም፤
የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፡፡
ወንጌል:- ዮሐ 3 ፥1-20
ቅዳሴ:- ቅዳሴ ማርያም