Wednesday, January 28, 2015

የእመቤታችን አስደናቂ ዕረፍት



ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
(ምንጭ፡ የቤልጂየም ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን መካነ ድር)
ስለ እመቤታችን ዕረፍትና ዕርገት ቊጥሩ 72 አርድዕት አንዱ የሚኾነው ቅዱስ ኢቮዲየስ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ስለነበረ በጥር ፳፩ የኾነ የቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍትና በነሐሴ ፲፮ የተከናወነ በዓለ ዕርገቷን በዐይኖቹ የተመለከተውንየቅድስት ድንግል ማርያም ኅልፈተ ሕይወትና ፍልሰትበሚል ርዕስ ጽፏል፤
http://fenoteabew.blogspot.com/
 
ድርሳን ዘደረሰ አባ ኢቮዲየስ ሊቀ ጳጳሳት ዘአንጾኪያ በእንተ ዕረፍታ ወፍልሰታ ለማርያም” Evodius of Rome, Homily on the Dormition The falling asleep of Mary “An instruction which our holy and in every wise honourable father Abba Evodius, the archbishop of the great city Rome, who was the second after Peter the apostle,…” (የእኛ ቅዱስ እና በማናቸውም ረገድ ብልኅ እና የተከበረ አባታችን፣ የታላቋ የሮም ከተማ ሊቀ ጳጳስ፣ ከሐዋርያው ጴጥሮስ በኋላ ኹለተኛው በኾነው የቀረበ መመሪያ፡፡ የኹላችንም እመቤት፣ እግዚአብሔርን የተሸከመች ቅድስት ማርያምን አስመልክቶ፤ በእግዚአብሔር ሰላም በግብጻውያን አቈጣጠር በ፳፩ኛው የጦቢ (ጥር) ወር ቅዱስ ሕይወቷን ያበቃችውን እመቤታችን አስመልክቶ የቀረበልን አስተምህሮ አሜን)፡፡



. “Now it came to pass at the hour of the light on the twenty-first of the month Tobi, …” (በጦቢ ወር በ፳፩ በብርሃን ሰዓት ላይ በነጋታው፣ እውነተኛው ቃል ክርስቶስ በኪሩቤል ሠረገላው ላይ ተቀምጦ እልፍ አእላፋት የሚቈጠሩ መላእክት ተከትለውት፣ በዙሪያው የብርሃን ኀይሎች ከብበውት እና ዳዊት በእሳት ሠረገላ ላይ ኾኖ ከፊቱ እየዘመረለት፣ መንፈሳዊ በገናን እየተመታ ከፍ ባለ ድምፅ ለኀያሉ ጌታችን ክብር እንዘምርለት አለ፡፡ መድኀኒታችን በመኻከላችን ቆመ፣ በሮቹ ተዘጉ ወደ ኹላችንም እጆቹን ዘረጋቸው፤ ብዙዎች ደቀ መዛሙርት በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፤ ሰላም ለእናንተ ይኹን አለን፡፡ ኹላችንም በአንድ ላይ ተነሥተን እግሮቹ ሥር ወድቀን የአምልኮት ምስጋናን አቀረብንለት፤ ርሱም በሰማያዊዉ በረከቱ ባረከን፡፡ መላእክቱም አሜን ብለው መለሱ፤ ርሱም ወደ አባቴ ጴጥሮስ በመዞርበረከት ልሰጣችኊ በመኾኑ መሠዊያዉን ጠብቀውአለው፤በዛሬው ቀን ከእናንተ መኻከል ታላቅ ስጦታ ማግኘት አለብኝአለ፡፡ እኛ ግን በእግሮቹ ላይ ተደፍተን አመለክነው እኛምከእናንተ መኻከል በዛሬው ዕለት ታላቅ ስጦታ ለመውሰድ እፈልጋለኊ ስትል ምን ማለትኽ ነውብለን አጥብቀን ለመንነው፡፡ መድኀኒታችንም ሲመልስልንከዓለም ኹሉ አብልጬ የመረጥኋችኊ ክቡራን ኅዋሶቼ ይኽቺ ቀን የአባቴ ዳዊት ትንቢት የሚፈጸምባት ቀን ናት፣ ንግሥቷ በወርቅ በተንቆጠቆጠ አልባሷ አጊጣ እና አሸብርቃ በቀኜ ትቆማለች (መዝ ፵፬፥፱)፡፡
ዛሬ ለዘጠኝ ወራት በምድር ላይ መኖሪያዬ ኾና የቆየችውን ድንግል እናቴን የምቀበልበት እና ከእኔ ጋር ወደ ሰማያት ሰማያዊ ቦታዎች ይዤያት በመውሰድ ለመልካሙ አባቴ በስጦታ የማስረክባት ቀን ነው፣ ዳዊትም እንኳንበኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፤ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ” (መዝ ፵፬፥፲፬) እንዳለ፤ ርሱም በመለኮታዊዉ እና ግሩም ድምፁ የኔ ውድ እናት ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መሓ ፪፥፲) የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ወደ እኔ ነዪ (መሓ፪፥፲፫) አላት፤ አንቺ ከቄዳር ልጆችም በላይ ውብ ቆንዦ ነሽ (መሓ ፩፥፭) አንቺ የተመረጥሽ ጎጆ ሆይ የመልካማ ርግብ መኖርያ ነሽ፤ አንቺ የተመረጥሽ የአትክልት ስፍራ ያለምንም ዘር እና የወንድ ሩካቤ መልካሙን ፍሬ ያፈራሽ (መሓ ፬፥፲፪) አንቺ የወርቅ መሶብ ሆይ መናው እውነተኛው መና እኔ እንኳን የተሰወርኹብሽ (ዘፀ ፲፮፥፴፫-፴፬) አንቺ ስዉር ቅርስ እውነተኛው ብርሃን የተሰወረብሽ እና ከአንቺም ውስጥ ወጥቶ በመገለጽ በሰው ልጆች ላይ የተትረፈረፈ ሀብት ያስገኘላቸው፡፡ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ የእኔ ውብ ርግብ ሆይ (መሓ ፮፥፱) የእኔ ቅድስት መርዐት (መሓ ፬፥፰) የእኔ ንጽሕት መስክ፣ ከእኔ ጋር ወደ አትክልት ስፍራው እወስድሻለኊ (መዝ ፸፩፥፮) ከርቤ እና ጣፋጭ ቅመማ ቅመሜን እደረድርልሻለኊ(መሓ ፬፥፲፬) ከበታችሽም እንድታርፊበት ያማረውን ምንጣፍ አነጥፍልሻለኊ፤ ማርያም እናቴ ሆይ አንቺ የተባረክሽ ነሽ ወደ ምድር ወልደሽ አምጥተሽኛልና፡፡

እኔ ኹሉን መጋቢ የኾንኹትን ያጠቡ ጡቶሽን የተባረኩ ናቸው፡፡ እንዲኹም በከፍታ ቦታዎች ወደሚገኙ ሰማያዊ ስፍራዎች ወስጄሽ በአባቴ በመልካም ነገሮች እመግብሻለኊ፡፡ እስከዚያው በጉልበትሽ ላይ ያስቀመጥሺኝ ድንግል እናቴ ማርያም ሆይ በኪሩቤል ሠረገላ ላይ በማኖር ከእኔና ከቸሩ አባቴ ጋር ወደ ሰማያት እወስድሻለኊ፡፡ በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ በወለድሽኝ ዕለት በከብቶች በረት ከላም እና አህያ ጋር በአንድ ላይ ከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯) እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ ኪሩቤልም በሰይፈ ነበልባላቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡ የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበት መሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡ እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደ ግብጽ ምድር እንደተሰደድሽው ኹሉ (ማቴ ፪፥፲፫-፲፰) መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ)፡፡



. “Now when we heard these things, as our Saviour was saying them to His virgin mother,…” (እነዚኽን ነገሮች ስንሰማ፣ መድኀኒታችን ለድንግል እናቱ እንደተናገረው፣ በሥጋ ሊወስዳት እንደፈለገ ኹላችንም ዐወቅን፡፡ ኹላችንም ፊታችንን አዙረን አምርረን አለቀስን፤ የኹላችንም እናት ቅድስት ድንግል ማርያምም ከእኛ ጋር በአንድ ላይ አለቀሰች፡፡ መድኀኒታችንም ለምን ታለቅሳላችኊ አለን? አባቴ ጴጥሮስምጌታዬ እና አምላኬ ሥርዓት አልበኞቹ አይሁድ አንተን በሰቀሉኽ ጊዜ በወደቀብን ከባድ ዐዘን የተነሣ ለጥቂት ቀናት አልቅሰን ነበር ግን በኋላ ላይ አንተ ከሞት በመነሣትኽ እጅግ ተደሰትን፤ አንተም ወደ እኛ ቀርበኸን በረከትኽን ለገስኸን፤ በሥጋ የአንተ እናት ብትኾንም የኹላችንም እናት ለኾነችው ወደ ድንግል እናትኽ ማርያም አደራ ጣልኽብን፡፡ አኹን ግን ርሷን ከእኛ የምትወስድብን ከኾነ የሚወድቅብንን ከባድ ዐዘን ለመቋቋም ስለማንችል ርሷን ከመውሰድኽ በፊት እኛኑ አስቀድመንአለው፡፡ መድኀኔ ዓለምምየእኔ የተመረጥኽ ጴጥሮስና በእኔ የተመረጣችኊ ሐዋርያቶች ሆይ በሙሉ ትቼያችኊ (ተለይቼያችኊ) እንደማልቀር እና ተመልሼ እንደምመጣ አልነገርኋችኹምን? (ዮሐ ፲፬፥፩-) ስለዚኽ ለማርያም ሞት ፈጽሞ ማልቀስ አይገባችኹም፤ ወደ እናንተ በፍጥነት ሳትመለስ በጭራሽ አልተዋትም፡፡

እኔም ራሴን ከእናንተ እንዳልሰወርኹት ኹሉ ድንግል እናቴም ፈጽሞ ራሷን ከእናንተ አትሰውርም፡፡ ስለዚኽ ኹልጊዜም ወደ እናንተ ስመጣ ድንግል እናቴን ከእኔ ጋር አብራ እንድትመጣ በማድረግ ነፍሳችኊ እንዲቀደስ አደርጋለኊአለ፡፡ እዚኽ ላይ አባቴ ጴጥሮስ እና የተቀሩት ደቀ መዛሙርት ለመድኀኒታችንአምላካችን እና ጌታችን ከነጭራሹ ፈጽሞ የሞትን ጽዋ እንዳትጋፈጥ ማድረግስ አይቻልም ነበርን?” አሉት፤ መድኀኒታችንምየእኔ ቅዱሳን ሐዋርያቶች ሆይ ይኼ ንግግር ከእናንተ በመምጣቱ በጣም ድንቅ ነው አላቸው፡፡ በመዠመሪያ የተናገርኹት ቃል ሊታበል ይችላልን? አይችልም አባቴ ከልክሏልና፡፡ ገና ከመዠመሪያውም ኹሉም ሥጋ የለበሰ ሰው ኹሉ ሞትን ማጣጣም ያስፈልጋቸዋል ብዬ ፍርድ ፈርጃለኊ (ዘፍ ፫፥፲፱)፡፡ እኔም የሰዎች ኹሉ ጌታ የኾንኹት በለበስኹት ሥጋ የተነሣ ሞትን ቀምሼ የሞትን ሰቈቃ ያጠፋኊትአለ (ሮሜ ፭፥፲፯)፡፡ አባቴ ጴጥሮስም በዚኽ ጊዜ ላይ እንደገናከአንተ ጋር እንድነጋገር ፍቀድልኝአለው፡፡ ጌታምተነጋገርአለው፡፡ አባቴ ጴጥሮስምጌታዬ ለእኛ በማዘን እመቤታችን የምቾታችን (የሐሤታችን) ምንጭ በመኾኗ ለጥቂት ጊዜ በሕይወት እንድትቆይ አድርግልንአለው፡፡ መድኀኒታችንም ሲመልስለት እያንዳንዱ ሰው በዚኽች ምድር ላይ የተቀመጠለት የቆይታ ጊዜ አለ፤ ጊዜው ሲደርስም ለአንዲት ሰዓትም እንኳን በተጨማሪ ለመቆየት አይቻለውም አለው፡፡ አኹን ስለዚኽ ለእናቴ የተቀመጠላት ጊዜ ዛሬ ይፈጸማል፡፡ አኹን ሰውነቷን አኑራ እና ከእኔ ጋር በክብር ወደ ሰማያት መኼድ ይገባታልና፤ የሰማያትን ሥርዓት ተመልከቱ፣ አባቴ የውድ ልጁ መቅደስን፤ እኔን ጨምሮ እየጠበቅናት ነውና፡፡ ወደ አባቴ ሳልወስዳት በፊት እራሴ እኔ በቅዱስ መሥዋዕት ከርሷ ጋር እንባርካችኋለንናአለን)፡፡
. “The women therefore that went with her, even the virgins that followed her, turned their face away, and all wept bitterly…” (ከርሷ ጋር በአንድነት ይኼዱ የነበሩትም ሴቶች ተከትለዋት የነበሩትም ደናግል ፊታቸውን አዙረው ኹሉም አምርረው በሲቃ ድምፅ አለቀሱ፤ ቅድስት ድንግል ማርያምም አብራቸው አለቀሰች፡፡ ቸሩ መድኀኒታችንምማርያም ድንግል እናቴ ሆይ ስለምን ታለቅሺያለሽ? አላት፤ አኹን ልቅሶሽን በመተው ለዘላለም ነዋሪ ወደኾነው ደስታ መኼድ አለብሽ አላት፤ ሐዘን እና ለቅሶሽን በመተው በሐሤት እና በደስታ ለዘላለሙ መኖር ይገባሻል፤ የምድር ነገሮች በሙሉ ትተሽ የሰማያት የኾኑትን መውረስ ይገባሻልና ድንግል ማርያምም ለመድኀኒታችን ስትመልስለትጌታዬ፣ አምላኬ እና ልጄ እንዴት ዐላዝን እና በልቤስ አላለቅስ? በጣም ብዙ ጊዜያት በሰው ልጆች ሞት በጣም ብዙ ቅርፆች እናዳሉት፣ ሊወስዳቸው ከመጣ በኋላም አስፈሪ እና አሰቃቂ ነገር እንዳለው ሲነገር ሰምቻለኊ፤ እነዚኽ ነገሮች ከኾኑ፣ እንዴት አላለቅስ እንዴት ብዬስ አስፈሪውን ቅርፁን ልመልከተው?” አለች፤ ጌታችን ኢየሱስምውዷ እናቴ ማርያም ሆይ ሞትን ፈጽሞ እንዳትፈሪው፣ ማንኛውንም የሞት ኀይል ለማውደም የሚችለው ከአንቺ ጋር አይደለምን? አላት፤ ብዙ ቅርጽ ያለው ጣዕረ ሞትን የዓለም ኹሉ ሕይወት እስትንፋስ የያዘው ከአንቺ ጋር እያለ እንዴት ትፈሪዋለሽን?” አላት፤ ጌታም በራሱ ራርቶ ራሱን ወደ ድንግል እናቱ አስጠግቶ እንባዎቿን ጠራርጎላት በመለኮታዊ ከናፍሮቹ ሳማት፡፡

ከዚያም ጌታ ኢየሱስ በመሠዊያዉ ላይ በመኾን ኹላችንንም ባረከን፣ የሰላም ሰላምታውን አቅርቦልን፣ አባቴን ጴጥሮስንፍጠን ወደ መሠዊያዉ ተመልከትና አባቴ ከሰማይ የላከልኝን ንጹሓት አልባሳትን አምጣልኝ ድንግል እናቴን ላልብሳት ምክንያቱም የርሷን ቅዱስ ሰውነት በምንም ዓይነት ከምድር የተገኘ ጨርቅ መሸፈን አይገባውምናአለ፡፡ከዚያም አባቴ ጴጥሮስ ያማረውን ውብ ሸማ፣ ንጹሕ፣ ቅዱስ፣ በጣም ውድ እና ጣፋጭ መዐዛ የሚረጨውን ይዞ መጣ፤ እጅግ ደማቅ ብርሃን የሚለቀውን ያማረ ሸማ ስንመለከት ኹላችንም በጣም ተደነቅን፡፡መድኀኔ ዓለምም ያማረውን ሸማ ከአባቴ ጴጥሮስ ላይ ተቀብሎት በራሱ መንገድ ዕጥፋቶቹን በመዘረጋጋት፤ድንግል እናቱን ጠርቷት፣ ተነሺ የእኔ ብራማ ርግብ ክንፎችሽ በወርቅ የተንቈጠቈጡት ወደ እኔ ነዪ አላት (መዝ ፰፯፥፲፫)፤የእኔ ንጽሕት እና እንከን የለሽ ጠቦት ወደ እኔ ነዪአላት(መዝ ፷፰፥፴፩):፡

. “And she arose, the queen of all women, Mary the Virgin, the mother of the King of kings, to go unto her beloved Son, our Lord Jesus Christ…” (የሴቶች ኹሉ ንግሥት፣ ድንግል ማርያም፣ የነገሥታት ንጉሥ እናት ወደ ተወዳጁ ልጇ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመኼድ ተነሣች፡፡ ኹላችንም ከተቀመጥንበት ተነሥተን እጆቿን እና እግሮቿን እያነባን ሰላምታን ሰጠናቸው፤ ከዚያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውድ ልጇ ሰላምታ አቅርቦላትወደ ዘረጋኹልሽ አልባሳት ውስጥ ግቢ እና ፊትሽን ወደ ምሥራቅ መልሺ እና ጸሎት አቅርቢ፤ ከዚያ በኋላ መጐናጸፊያው ላይ ጋደም በይ እና በምድር ላይ ለተወለዱ ሰዎች በሙሉ ጸሎትሽን አሟይአለ፤ የሴቶች ኹሉ ልዕልት፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የነገሥታት ኹሉ ንጉሥ እናት ከተቀመጠችበት ተነሥታ መድኀኒታችን በእጆቹ ወደ ዘረጋላት መሸፋፈኛ መኻከል ገባች፡፡ በቆመችበት ፊቷን ወደ ምሥራቅ አግጣጫ አዙራ በሰማይ ነዋሪዎች ቋንቋ ጸሎቷን አቀረበች፡፡ ጸሎቷንም እንደጨረሰች አሜን አለች፤ እኛም ኹላችንም ከተቀመጥንበት ተነሥተን አሜን ብለን መልስ ሰጠናት፡፡ ከዚኽ በኋላ በመሸፋፈኛ አልባሳቱ ላይ ጋደም ብላ እጆቿን ተደግፋ ወደ ምሥራቅ አግጣጫ ፊቷን አዞረች፡፡

ከዚያም መድኀኒታችን ከርሷ ጋር በቤተ መቅደስ ሲያገለግሉ ከነበሩትና መድኀኒታችንን እስከ እግረ መስቀል ሲከተሉ ከነበሩ ደናግል ጋር በአንድ ላይ እንድንጸልይ ለጸሎት እንድንቆም አደረገን፡፡ ክርስቶስ በተሰቀለበት ጊዜ ሴቶቹ ተከትለዋት መጥተው ነበር፡፡ እኛም በቤተ መቅደስ ለምን ማገልገል እንዳቆሙ ስንጠይቃቸው? እነርሱም የእግዚአብሔር አብ ቃል ክርስቶስ በተሰቀለበት ቀን ኹሉም ቦታዎች ሲለወጡ ተመልክተን ነበር አሉን፡፡ ፀሓይ ጨልማ ነበር፣ ጨረቃ ደም መስላ ነበር ከዋክብትም ከሰማያት ወደ ምድር ወድቀው ነበር፡፡ እኛም በጣም ፈርተን የቅዱሳን ኹሉ ቅዱስ ወደኾነው የጌታ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሸሽተን ገባን በሩንም ጥርቅም አድርገን ዘጋነው፡፡ ወዲያውኑም ኀይለኛ መልአክ ከሰማይ በታላቅ ቁጣ በእጁ ውስት የሚያብለጨልጭ ሰይፍ ይዞ ወደ ምድር ሲወርድ ተመለከትን፣ በያዘው ሰይፍም መጋረጃውን መኻል ለመኻል ከላይ ወደታች እኩል በእኩል ቀደደው (ማቴ ፳፯፥፶፩)፡፡ ከዚያም ታላቅ ድምፅኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ ነቢያትን የምትገድል ወደ ርሷ የተላኩትንም የምትወግር ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድኊ! አልወደዳችኹምም እነሆ ቤታችኊ የተፈታ ኾኖ ይቀርላችኋል” (ማቴ ፳፫፥፴፯) የሚል ሰማን እንደገና ስንመለከት ለመሠዊያው ተመድቦ የነበረው መልአክ በመሠዊያው በላይ ሰይፉን ይዞ በታላቅ ቁጣ ሲበርር ተመለከትን፤ እነዚኽ ነገሮች በሙሉ ሲኾኑ ባየን ጊዜ፣ ጌታ በሰዎቹ በጣም እንደተቆጣና በርግማን ሥር እንዳንወድቅ በማሰብ ከእኛ ጋር ወደነበረችው እናቱም በፍጥነት እንደመጣን ዐወቅን፣ ይኽነንም መጋረጃውን ከቀደደው የጌታ መልአክ አፍ ሰማንአሉ (ማቴ ፳፯፥፶፩)፡፡



፲፩. “The twelve virgin s therefore and all the women also who were with us, were all weeping with us together,…” (ዐሥራ ኹለቱ ደናግል እና ከእኛ ጋር የነበሩት ሴቶች በሙሉ ድንግል ማርያምን በዙርያዋ ከብበን የተማርነውን የሰማያዊ ምስጋና መዝሙር ስንዘምር ቆመን ስናለቅስ ነበር፡፡ ክርስቶስም ለእናቱ ክብር እጆቹን በጉንጮቿ ላይ አድርጎ ከጐኗ ተቀምጦ ነበር፡፡ ለረዥም ጊዜ በዝማሬ ላይ ሳለን ክርስቶስ ለእናቱ ሰላምታ አቅርቦላት ወደ ውጭ ይዞን ወጣ፡፡ ድንግልምኢየሱስ ሆይ እውነተኛው ያለምንም ነውር ነቀፋ የወለድኹኽ ልጄ፣ የኀያሉ እግዚአብሔር ልጅ እና ውዱ ልጄ ልለምንኽ፣ የወለድኻትን እናትኽን እንዳትረሳት፣ ጌታዬ ሆይ፣ የሞት ጥላ እንዳይቀርበኝ፤ ውዱ ልጄ ሆይ የአምባገነኑ የሞት ኀይሎች እና የድቅድቁ ጨለማ ሥልጣናት ይርቁ ዘንድ፡፡ የብርሃን መላእክት ይቅረቡኝ እንጂ ሞትን የማያውቁት ትሎች እንዳሉ ባሉበት ይኹኑ፡፡ የውጭው ጨለማ ብርሃን ይኹን፡፡ የሐሰት ከሳሾች አፍ ይዘጋ፡፡ በጥልቁ እንጦርጦስ የሚገኘው እሳት የሚተፋው ዘንዶ ወደ አንተ ስመጣ ሲመለከት አፉ የተዘጋ ይኹን፡፡ ውዱ ልጄ ሆይ የጥልቁ እንጦርጦስ አዛዦች ከእኔ እንዲሸሹ እና ነፍሴን እንዳያስፈራሯት እዘዛቸው፡፡ በእነዚኽ መንገዶች የሚገኙት አደናቃፊ ድንጋዮች ከፊቴ ይውደሙ፡፡ በመጥፎ ዐይኖቻቸው የሚያዩኝን በቀለኞችን ከልለኝ፡፡ ልክ እንደ ባሕር ማዕበል የሚናወጠው የሚንቀለቀለው የእሳት ወንዝ፣ ጻድቃን እና ኀጥኣንን ለኹለት የሚከፍለው በማልፍበት ጊዜ ነፍሴን ፈጽሞ እንዳይነካት፤ ምንም ኀፍረት በሌለበት ፊቴ አመልክኻለኹና ከዘመናት እስከ ዘመናት ኀይል እና ክብር የአንተ ናቸውአሜን)፡፡

፲፪. “And our Lord Jesus Christ said to His mother with His gentle voice, Be of good cheer, O Mary my mother…” (ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን ድንግል ማርያም ለስለስ ረጋ ባለ አስደሳች አንደበቱ ማርያም እናቴ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አላት፡፡ እነዚኽ ኹሉ ነገሮች በአንቺ ውስጥ ፈጽሞ ቦታ ስለሌላቸው ከአንቺ አርቄ አባርርልሻለኊ፤ በእነርሱ ፈንታ ለዘላለሙ ማረፊያሽ የኾኑትን የሰማያዊ ማረፊያ ቦታዎች እና በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም የሚገኙትን መልካሞች ነገሮችን አዘጋጅቼልሻለኊ፡፡ አካልሽ በውስጡ የሚሸፋፈንበት ከገነት የመጣውን ሰማያዊ መሸፈኛ እና እጅግ ያበቡትን የዘንባባ ዝንጣፊዎች አዘጋጅቼልሻለኊ፡፡ ቅዱስ ነፍስሽን ከእኔ ጋር ወደ ሰማይ በመውሰድ ለመልካሙ አባቴ በስጦታነት አበረክታታለኊ፣ እኔን የወለድሽኝ አንቺ ቅድስት ሆይ ከስጦታዎች ኹሉ እጅጉን ከፍ ያልሽ ስጦታ ነሽናአላት፤ ጌታችን ሐዋርያቱንእኔ የዓለም ሁሉ ሕይወት እስትንፋስ ባለኹበት ሞትን ማየት ስለማይገባት የውድ እናቴ ነፍስ መሰናበቻዋ ጊዜ በመቃረቡ ለጥቂት ጊዜያት ወደ ውጭ እንውጣአላቸው፡፡ እነሆ አኹን እኛን በመጠበቅ በአንድ ላይ ኹሉም የሰማያት ኀይሎች ኹሉ ተሰብስበዋልና፤ ስለዚኽ ርሷ ጋደም ብላ እንዳለች ትተናት ጌታን ተከትለን ኹላችንም ወደ ውጭ ወጣን፤ ከርሷ ጋር የተሰበሰቡት ደናግል ዮሐና እና ሰሎሜ እንዲኹም ኹሉም ታማኝ ሴቶች ሊያገለግሏት በውስጥ ቀሩ፡፡ ጌታችን በመግቢያው በር ላይ በውጭ በሚገኝ አንድ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ ሳለ ኹላችንም ከብበነው በዙሪያው ቆምን፡፡ ወደ ሰማይ ተመልክቶ በከፍተኛ ድምፅሞት ሆይ መኖሪያኽ በስተደቡብ በሚገኙት የማከማቻ ስፍራዎች የኾነው ድል ነሥቼኻለኊና ሥጋ በለበሱ ፍጡራን ላይም በሙሉ ሥልጣን ሰጥቼኻለኊ እና ወደ ድንግል እናቴ ና፣ ቅረባት ትመልከትኽ ግን ማርያም እናቴ ምንም ልታይኽ እስከማትችልበት ጊዜ ድረስ ማቃጠልኽ እና አሸናፊነትኽ ይውደም፡፡ ከዚያ በኋላ ግን (እናቴ ካረፈች በኋላ) ለዘላለሙ የምትለብሰውን አስፈሪ ቅርጽ እና ማቃጠልኽን እንዲኹም አሸናፊነት መልሰኽ ተጐናጸፍ፡፡ በአፍታ ቅጽበት እና በዐይን ብልጭታ ከሰው ልጆች ኹሉ ስሙ እጅግ አስፈሪ የኾነው ሞት ቀረበ፡፡ ልክ በዐይኖቿ እንዳየች ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታ ልጇ ተቀምጦበት ወደነበረው ቦታ መጥታ በዕቅፉ ውስጥ ወደቀች፡፡ የእግዚአብሔር ቃልም በነበርንበት ቦታ ከመኻከላችን ተቀምጦ ሳለ ሰማይ እና ምድርን መላቸው፡፡ እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ የከበረ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው፣ ይኽም ለቅዱስ አካሏ ማኖሪያ ቦታ እስኪያዘጋጅ ድረስ ነበር፡፡ ኹሉም በዙሪያዋ ከበው የነበሩት ሴቶች ዕረፍቷን በተመለከቱ ጊዜ እጅግ ዐዝነው አለቀሱ፡፡ ሰሎሜም ወደ ውጭ ወጥታ በጌታዋ እግር ላይ ተደፍታጌታዬ አምላኬ ተመልከት ውድ እናትኽ ዐርፋለችብላ አመለከችው፡፡ ዛሬ ታላቅ ዐዘን እና መነጠል የወደቀብን ለእኛ ወዮውልን፡፡ አንተ በአጠገቧ ብትኖር ኖሮ አትሞትም ነበር፡፡ ጌታ ኢየሱስምእናቴ ድንግል ማርያም አትሞትም ይልቁንም ለዘላለም ትኖራለች፤ የእናቴ ሞት ሳይኾን የዘላለም ሕይወት ነው እንጂአለ፡፡ ቅዱሱ አመስጋኝ ዳዊትን በመንፈሳዊ በገናው ጮኾ በመዘመርበጌታ ፊት የቅዱሳኑ ሞት እጅግ የከበረ ነው” (መዝ ፻፲፭፥፲፭) የነገሥታት ኹሉ ንጉሥ የኾነው የክርስቶስ እናት ማርያም ደስ ይበልሽ፤ ይኽ ስለ እውነተኛዋ ንግሥት ማርያም የተናገርኩት ትንቢት የተፈጸመበት ቀን ነው” (መዝ ፵፬፥፱) በማለት ዘመረ)፡፡
 

No comments:

Post a Comment