ሕልመ ሌሊት
በጠለቀ እንቅልፍ ላይ
ሳሉ
የሚከሠት
ሕልመ
ሌሊትን
እንደ
ኃጢአት
እንዲቆጠርና
እንዳይቆጠር
የሚያደርጉ
የተለያዩ
ሁኔታዎች
አሉ::
ስለዚህ
ሕልመ
ሌሊትን
በጥቅሉ
ኀጢአት
ነው
ወይም
አይደለም
ማለት
አይቻልም::
ነገር
ግን
እንደ ኀጢአት
እንዲቆጠር የሚያደርጉ ሁኔታዎችን በመጠኑ መዘርዘር ይቻላል::
፩/. አጋንንት የሰውን ልጅ በተኛበት ክፉ ክፉ ሕልም በማሳየት ይፈትኑታል:: አንድ ጊዜ የተራቆተ የሴት ገላ; በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ወንድና ሴት አለሌና ባዝራ እየሆኑ ሲጨዋወቱና ሲደራረጉ በምትሐት ያሳዩታል:: በዚህ ጊዜ እርሱም በዝሙት ሐሳብ ይሳብና በሕልሙ ዝሙት ሲፈጽም ያድራል:: በዚህ መልኩ የተከሠተ ሕልመ ሌሊት "ጸዋግ" ወይም "ኅሡም" ሕልም ይባላል:: ክፉ
ወይም ጥፉ ሕልም ማለት ነው::
በዚህ መልኩ አጋንንት ሰውን እንደሚዋጉት
በመጽሐፈ መነኮሳት እንዲህ ተጽፏል:: "ይትቃተልዎ ሰይጣናት በመዓልት
በሕሊናት እኩያት ወበሌሊት በአሕላማት ኅሡማት" በአማርኛ "ሰይጣናት
የሰውን ልጅ ቀን ቀን ክፉ ሐሳብ በማሳሰብና በማሠራት በሌሊት ደግሞ ዝሙት የሞላበት አስጸያፊ ሕልም በማሳየት ይዋጉታል"