ሰማዕት
የሚለው ቃል ከግዕዙ “ሰምዐ” ካለው የወጣ ነው፡፡ትርጉሙም መሰከረ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሰማዕት ላለው ቃል መነሻው ምስክር ማለት
ነው፡፡“በኢየሩሳሌም ፣ በይሁዳ ፣በሰማርያ እሰከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” ሐዋ 1፥8-22 እንዳለው፡፡ እንግዲህ
ምስክር የሚለው ቃል በመጀመሪያ ለሐዋርያት የተሰጠ ስም ሲሆን በኋላም ሀይማኖታቸውን እንደ ሐዋርያት ለሚገልጡ ምእመናን የተሰጠ
ስያሜ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ደግሞ ምስክርነታቸውን የገለጡት በማስተማር ብቻ ሳይሆን ስለሚያስተምሩት ትምህርት(ወንጌል) ትክክለኛነት
በፈቃዳቸው ሰማዕት እስከመሆን ደርሰው ነው፡፡ስለዚህ ሰማዕትነት ማለት ስለሃይማኖት
ሲባል በፈቃድ ሞትን(መከራን)
መቀበል ማለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሰማዕትነት ሶስት ነገሮችን የያዘ ነው፡፡
Thursday, April 23, 2015
Monday, April 20, 2015
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዐረፉ |

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የባሕር ዳር፤ የአዊና የመተከል አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተወለዱ በ84 ዓመታቸው ሚያዝያ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ጠዋት ዐርፈዋል፡፡
ሐሙስ ሚያዝያ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. በባሕር ዳር ከተማ የተገነባውን መንፈሳዊ ኮሌጅ በቅዱስ ፓትርያርኩ ካስመረቁ በኋላ ድንገት በመታመማቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደው ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆይም ሚያዝያ 10 ቀን ጠዋት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ሥርዐተ ቀብራቸው እሁድ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡
Wednesday, April 15, 2015
የትንሣኤው ትርጉምና የሰሙነ ፋሲካ ዕለታት |
ትንሣኤ የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡
መገኛ ቃሉም ተንሥአ = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡
ትንሣኤ ማለት = መነሣት፣ አነሣሥ፤ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡ ትንሣኤ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም አምስት ክፍሎች አሉት፡፡
አንደኛው ትንሣኤ ኅሊና ነው፡፡ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር ነው፡፡
ሁለተኛውም ትንሣኤ ልቡና ነው፡፡ የዚህም ምስጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡
ሦስተኛው ትንሣኤ ለጊዜው የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡
አራተኛውትንሣኤ የክርስቶስ በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት ነው፡፡ የትምህርታችንም መሠረት ይኸው ነው፡፡
ዐምስተኛውና የመጨረሻው የትንሣኤ ደረጃም የባሕርይ አምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ መሠረት ያደረገ ትንሣኤ ዘጉባኤ ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ይሆናል፡፡
|
Wednesday, April 8, 2015
በሰሙነ ሕማማት የሚነሡ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው | ![]() | ![]() |
መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓዋጅ ከሚጾሙት አጽዋማት መካከል ዐቢይ ጾም፤ ጾመ ኢየሱስ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ አሁን በጾሙ መጨረሻ ሳምንት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሕማምና ሥቃይ እንዲሁም እንግልት በምናስብበትና የጨለማውን ዘመን በምናስታውስበት ጊዜ /ሰሙነ ሕማማት/ ላይ እንገኛለን፡፡ ስለ ሰሙነ ሕማማት ስናነሣ በምእመናን ዘንድ የሚነሡ አንዳንድ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እኛም እነዚህን ጥያቄዎች ለሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በማቅረብ የሰጡንን ምላሽ ይዘን ቀርበናል፡፡ |
Subscribe to:
Posts (Atom)