መንፈሳዊ አገልግሎት ሲባል ሁሌም የምትታወሰው ቤተ-ክርስቲያን ናት፡፡ይህ አገልግሎት የቤተ ክርስቲያንን ህይወት በእጅጉ
የተንተራሰ ሠፊ የቅድስና መንገድ ነው፡፡ከዚህ ህይወት የምንረዳው
አንዱና ትልቁ ነገር የቤተ ክርስቲያን ህይወት የተጋድሎ ህይወት መሆኑን ነው፡፡ይህ ትግልም ለግል ክብርና ዝና ወይም እንደ ህልም
ታይቶ ለሚጠፋው ለዚህ ዓለም ሥልጣን እና ምቾት ሳይሆን በስጋ የተገለጠው እግዚአብሔር ወልድ የገለጠውን የመዳን ምስጢርና እውነት
ለመመስከርና ይህን የእውነት ቃል ለሰዎች ለማዳረስ የሚደረግ ተጋድሎ ነው፡፡
እንግዲህ በዚህ ህይወት ውስጥ ብዙ ተቃራኒዎች አሉ፡፡ ነገር ግን ዛሬ ማንሳት የፈለግነው ስለተቃራኒ ፈተናዎች ሳይሆን
መንፈሳዊ አገልግሎት ራሱ የዲያብሎስ የቅንብር ስራ ሊሆን እንደሚችል እና ብዙዎቻችን በዚህ መንፈሳዊ መሰል አገልግሎት ተጉዘን ፍጻሜያችን
ግን ምን ሊሆን እንደሚችል እንመለከታለን፡፡ዲያብሎስ የሰውን ልጆች ከጽድቅ መንገድ ማራቅ የተለመደ ስራው ነው፡፡ የሰው ልጆች ዕለት
ዕለት ወደ አምልካቸው ወደ እግዚአብሔር በሚያደርጉት የቅድስና ጉዞ እንቅፋት በመሆንም ሊያገኙት ከነበረው ክብር እና ጸጋ ፈጽሞ
እንዲለዩ ያደርጋል፡፡እንግዲህ ይህንን ተግባሩን በተለያዩ መንገዶች እና ስልታዊ በሆኑ ዕቅዶች ያከናውናቸዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ
ተስፋ በማስቆረጥ፣ጥርጣሬ በመትከል፣በማዘግየት፣መልካም ምግባራትን