የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አትጥራ

ከዚህ ቀጥለን ሰዎች ስሙን በከንቱ የሚጠሩባቸውን ሁኔታዎች ባጭር ባጭሩ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
ሀ.መሐላ፡- መሐላ ስመ እግዚአብሔር በከንቱ ከሚጠራባቸው መንገዶች አንዱ ነው፡፡በዘመነ ብሉይ የአምልኮ ጣዖትን ከንቱነት ለመግለጥ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቡ በስሙ እንዲምሉ ያዝ ነበር(ዘዳ 6:13፤ኢሳ 45:23)፡፡በሐዲስ ኪዳን ደግሞ በእግዚአብሔር መማል ብቻ ሳይሆን መሐላ በጠቅላላው የተከለከለ መሆኑን መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡ይህ የሐዲስ ኪዳን ዘመን አረማዊነት ና አምልኮ ጣዖት ጠፍቶ ወንጌል የተሰበከበት፣ክርስት ና በዓለም ሁሉ የታወቀበት ነውና መማል አላስፈለገም፡፡ስለዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ #ከቶ አትማሉ፤…ቃላችሁ አዎን፣አዎን ወይም አይደለም፣አይደለም ይሁን፣ከዚህም የወጣ ከክፉው ነው$በማለት መሐላን ከልክሏል (ማቴ 5:34-37)፡፡ስለሆነም በየሰበቡ የእግዚአብሔርን ስም፣የቅዱሳንን ስም፣የመላእክትን ስም ሁሉ እየጠሩ መማል የተከለከለ ነውና ከዚህ መቆጠብ ይገባል፡፡በተለይም በየአጋጣሚው ስመ እግዚአብሔርን እየጠሩ መማል የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መጥራት መሆኑንበሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡