ስያሜው የቅዱስ ያሬድ ሲሆን በዚህ ቀን ስለ ቅን አገልጋዮች ለአገልግሎት
የሚያገለግሉበትን ጸጋ ለሰዎች ሁሉ የሚሰጥ “ወሀቤ ጸጋ” አገልጋዮቹን “ገብርኄር” እያለ ዋጋ የሚሰጥ አምላክ መሆኑ እየታሰበ ይመለካል፡፡
የእለቱ
ስርዓተ አምልኮ
ዘቅዳሴ
በገባሬ
ሰናይ ዲያቆን 2ጢሞ 2 ፥ 1-16
በንፍቅ
ዲያቆን 1 ጴጥ 5 ፥ 1-12
በንፍቅ
ቄስ የሐዋ 1 ፥
6-9
ምስባክ፡-
ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፤
ወሕግከኒ በማዕከለ ከርስየ፤
ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር
ዐቢይ፡፡
አማርኛ
፡- አምላኬ
ሆይ ፈቃድህን ለመናገር ወደድኩ
ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው
በታላቅ ጉባኤም ጽድቅህን
አወራሁ (ተናገርኩ)፡፡
ትርጉም፡- አቤቱ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን (ህግህን፣ ወንጌልህን) እናገር ዘንድ
ወደደኩ ህግህ በልቦናዬ ተጽፎ ይኖራል፣ ቸርነትህንም በብዙ ጉባኤ ነገርሁ፡፡
ወንጌል፡- ማቴ 25 ፥ 14-31
ቅዳሴ፡- የባስልዮስ ቅዳሴ
No comments:
Post a Comment