Saturday, March 14, 2015

፭ተኛ ሳምንት ደብረ ዘይት





ስያሜው አንደቀደሙት ዕለታት ሁሉ የቅዱስ ያሬድ ስያሜ ሲሆን በዚህ ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ሁለተኛ በግርማ መለኮት በክበበ ትስብእት (በመለኮታዊ ግርማው በሰው መጠን)  እንደሚመጣ የዓለምም ፍፃሜው እንዴት እንደሚሆን ለሐዋርያት በደብረ ዘይት ማስተማሩን እንዲሁም በክብር ያረገው ጌታን ለሚጠባበቁ ዋጋቸውን፣ ላልተቀበሉትም ፍዳቸውን ሊከፍል የምድርን ስርዓት ሊሽር ሰማይን እና ምድርን አሳልፎ ለወዳጆቹ መንግስቱን ሊያወርስ፣ የቅዱሳኑንም እንባ ከአይናቸው ሊያብስ ፣ ኃጥአንን ሊወቅስ ፣ ፃድቃንን ሊያወድስ (ቡሩካን ብሎ) መምጣቱን እያሰበች ቤተ ክርስቲያን ፈጣሪዋን ታመልካለች፡፡
የእለቱ ስርዓተ አምልኮ
ቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች
በገባሬ ሠናዩ ዲያቆን      1 ተሰ 4፥13 
በንፍቁ  ዲያቆን          2ጴጥ 3፥7-15
በንፍቅ ቄስ              የሐዋ ሥራ 24፥1-22
ምስባክ                እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ፤
                      ወአምላክነሂ ኢያረምም ፤
                      እሳት ይነድድ  ቅድሜሁ፡፡    መዝ 49 ፥ 3          
ወንጌል                 ማቴዎስ 24፥1-36
ዘቅዳሴ                 ዘአትናቴዎስ

No comments:

Post a Comment