Saturday, February 28, 2015

3ተኛ ሳምንት ምኵራብ



ምኩራብ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ነው፡፡ ምኵራብ ማለትም ሰቀላ መሰል አዳራሽ ማለት ነው። አይሁድ ስግደትና መሥዋዕታቸውን የሚያቀርቡት በኢየሩሳሌም ባለው መቅደስ ብቻ ነው ብለው ቢያምኑም (ዮሐ 420) ፤በየተበተኑበት ቦታ ምኩራብ እየሠሩ ትምህርተ ኦሪትን በመማር ሃይማኖታቸውን ያፀኑ ነበር። ከአስር በላይ አይሁዳውያን በአንድ መንደር  ካሉ  አንድ ምኵራብ  እንዲሰራላቸው የአይሁድ ህግ ያዛልአይሁድ በምኲራቦቻቸው የሕግንና የነቢያትን መጻሕፍት /የብራና ጥቅሎች/ በአንድ ሣጥን ውስጥ ያስቀምጣሉ፡፡ በመሆኑ የጸሎት ሥፍራዎቻቸውን ለትምህርትና ለአምልኮ ይጠቀሙባቸዋል፡በምኩራብ አይሁድ ይጸልያሉ፣ ይማራሉ፣ ያስተምራሉ በአጠቃላይ ስርዓተ አምልኮን ይፈጽማሉ፡፡ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያ ምራብ ለማስተማር በገባ ጊዜ ግን በተቃራኒው መሸጫ እና መለወጫ ሆነው ርግብንና በሬን ሲነግዱ እንደነበረ ተጽፏል፡፡ጌታችንም ይህንን አይቶ እንደፈለጋችሁ ሁኑ ብሎ ዝም አላላቸውም፡፡
ይልቁንም  የገመድ ጅራፍ  አበጅቶ እየገረፋቸው የርግብ ሻጮችንም ወንበር  እየገለበጠ አሳደዳቸው እንጂ ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል እናንተ ግን የወንበዴዎ ዋሻ የቀማኞች መሸሸጊያ አደረጋችሁት ብሎ በማለት ለጸሎት ያይደለ ለንግድ የገቡት ከቤቱ እንዲወጡ አድርጓል ይህች ምራብ  ዛሬይቱ ቤተክርሰቲያን ምሳሌ ነች፡፡ 

ከዚህም የተነሳ ይህ ሳምንት የቤተክርስቲያን ጠመንፃት ሳምንት ይባላል፡፡ ምክንያቱም ከቤተክርስቲያኑ ወይም ከምራብ ለቤቱ /የማይገቡትን ሰዎች እና ሰርአታቸውንም አውጥቶ ቤቱን አንጽቷልና፡፡ዮሐ 2÷12 አንድም ቤት የተባለው የእኛ ሰውነት ነውሸቀትም የተባለው ክፉ ስራ፣ተንኮል እና ኃጢአት ነው፡፡ ስለዚህ ቤት የተባለውን ሰውነታችንን በንሰሐ ካልታጠብን ለእግዚአብሔር ማደሪያ የሚገባ ካላደረግነው እግዚአብሐሔር ከዕለታት አንድ ቀን ገርፎ የሚያስወጣን መሆኑነን የሚገልፅ ነው፡፡ስለዚህ ከአሁኑ ንስሃ ገብተን ልንሰናዳ ያስፈልጋል፡፡


በዚህ ሳምንት ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ከተናገራቸው ትንቢት መሀከል መዝ 68÷9 ያለው ኃይለ ቃል ይዘከራል፡፡ ይኸውም “የቤትህ ቅንዓት በልታኛለች እና የሚሰድቡህም ስድብ በላዪ ወድቋልና ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት ለስድብም ሆነብ፡፡” የሚል ነው፡፡ እንግዲህ ቤት የተባለው በዋናነት  የስሙ መቀደሻ  የክብሩ መገለጫ ቤተ መቅደሱ ሲሆን በሁለተኛነት ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነው የእኛ ሰውነት ነው፡፡ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ግን ቤተ መቅደስ እና ስርዓ ተሽሯል በአዲስ ኪዳን ግን ቤተ መቅደስ የለም ሲሉ የደመጣሉ፡፡ ጌታችን ግን ስርዓት የሚያፈርሱት አባረራቸው እንጂ ቤቱን አላፈረሰም ይህም ለቤቱ እና ለስርዓቱ ቀናተኛ አምላክ መሆኑን እነጂ ህጉን ሊሻር ስርኣቱንእና ቤቱን ሊያፈርስ የመጣ መሆኑን አያሳያም፡፡ ስለዚህ ይህ ሳምንት የቤተ ክርሰቲያን ክብርና ቅድስና በስፋት የሚነገርበት ሳምንት ሲሆን በአንጻሩ እግዚአብሔር ጅራፍ በተባለው መቅሰፍት ገርፎ ሳያወጣን በፊት በንስሐ መመለስ እንደሚገባን የኒነገርበት ሳምንት ነው፡፡

የዕለቱ ስርዓተ አምልኮ
ዘቅዳሴ 
  ቈላስ    2÷16 - ፍ፤ም   እንአግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለበዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም  አይፍረድባችሁ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና አከሉ ግን የክርስቶስ ነው፡፡……………….. እስከ ፍጻሜ ያንብቡ፡፡

  ያዕቆ  2÷14 - ፍ፤ም     ወንድሞቼ ሆይ እምነት አለኝ የሚል ስራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር  ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ ከእናንተ አንዱም በደኅና ሂዱእሳት ሙቁ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያሰፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል? እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው፡፡……………… እስከ ፍጻሜ ያንብቡ፡፡
  ግብ፣ሐዋ  10 ÷ 1-9  በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱም ከቤተሰቦዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት  የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ፡፡….እስከ ፍጻሜ ያንብቡ፡፡ 
          ምስባክ        እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ፤
                        ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ፤
                        ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፈስየ፤
                  ትርጉም
                        የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፤
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቋልና፤
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፤
ወንጌል ዮሐ 2 ÷12 - ፍ.ም    ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ በዚያም ጥቂት ቀን ኖረ፡፡ የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ………..እስከ ፍጻሜ ያንብቡ፡፡  


                   የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)

ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡

ትርጉም:- ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው ፡፡ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለ የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው፡) ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ

No comments:

Post a Comment