Thursday, April 30, 2015

በሊቢያ በአይ ኤስ አይ ኤስ ስለተሰዉ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች የአኀት አብያተ ክርስቲያናት አባቶች መልዕክት

€œለገዳዮቹ ጸልዩ፤ ይቅርም በሏቸው፡፡€ /ብጹዕ አቡነ አንጄሎስ በኮፕት ኦርቶዶክስ የታላቋ ብርቲያንያ ሊቀ ጳጳስ/

001abune angeloአሸባሪው አይ ኤስ አይ ኤስ 30 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን መግደሉንና ለዚህም ሓላፊነቱን መውሰዱን ተናግሯል፡፡ ክርስቲያኖቹን በመግደሉ ይቅር እንለዋለን፤ እንጸልይለታለንም፡፡ በማለት ብፁዕ አቡነ አንጄሎስ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላላፈዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ አንጄሎስ አሸባሪው ቡድን በፈጸመው ድርጊት የተሰማቸውን ሐዘን ሲገልጹም €œአይ ኤስ አይ ኤስ በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ ክርስቲያኖቹን ሲሰዋቸው የሚያሳያውን ምስል ወድምጽ በሁለት ቅጂ በኢንተርኔት ለቋል፡፡ በለቀቀው ምስል ወድምጽም 30 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ተገድለዋል፡፡
ክርስቲያኖች እንደመሆናችን ርኅራኄና ሰብዓዊነት ስለሌላቸው ሰዎች ድምጻችንን እናሰማለን፡፡ እንደ ክርስቲያን 21 የኮፕት ክርስቲያን ወንድሞቻችን በሊቢያ ሲገደሉ ሰማዕትነታቸውን አድንቀን፤ በእምነትም ተቀብለን ነበር፡፡ ይህንን ያደረግነው ለኛ ጥሩ ስለሆነ ብቻም አልነበረም የሃይማኖታችን ግዴታ ስለሆነ ጭምር እንጂ፡፡ በዚህ ዓለም በተለይም ለኛ ጠላቶቻችን ለሆኑት ይህንና ተመሳሳይ ድርጊት ለሚፈጽሙብን ለወንዶቹም ለሴቶቹም እንጸልያለን፡፡ ልቦና ሰጥቷቸው ይጸጸቱ ዘንድ፤ ምናልባትም እግዚአብሔር የሰው ልጅን ሲፈጥር ቅዱስና ልዩ አድረጎ በመሆኑ በፈጠራቸው በጥንተ ተፈጥሮ መንፈሳቸው ይጸጸቱና ይመለሱ ይሆናል፡፡€ ብለዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ አንጄሎስ በመቀጠልም €œእኛ ለነዚህ ነፍሳቸው ለተጨነቀችባቸውና በጭካኔ ለተሞሉት ሰዎች ልቦናቸው እንዲመልስላቸው እንጸልያለን ንጹሐንን ገድለዋልና፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ለሰማዕታቱ ቤተሰቦች፤ ለሕዝቡ ጽናትና ጥንካሬ እንዲሰጣቸው እንጸልያለን፡፡ እኩይ ድርጊታቸውን የማያውቁ በዓለም ያሉ ሕዝቦች ሁሉ በዚህ አሳዛኝ ድርጊት ሕይወታቸው እንዳይቀጠፍ ይጠንቀቁ፡፡ በየካቲት ወር በተመሳሳይ ሁኔታ ዓለም አቀፍ አሸባሪው አይ ኤስ አይ ኤስ በድምጽ ወምስል ባሰራጨው መረጃ 21 የግብጽ ኮፕት ክርስቲያኖች ሲታረዱ አይተን ነበር፡፡ ያ ሐዘናችን ሳይወጣ የኢትዮጵያውያንን መገደል አየን፤ ሰማን፤ ጥልቅ ሐዘንም ተሰማን፡፡€ሲሉ በአሸባሪ ቡድኑ የተፈጸመው ዘግናኝ ድርጊት ከሰብአዊ አስተሳሰብ ያፈነገጠ መሆኑን ሐዘን በተሞላበት ስሜት ገልጸዋል፡፡

€œንጹሐንን ስለ ሃይማኖታቸው ብሎ በግፍ መግደል ፍትሃዊና ተገቢ አይደለም ያሉት ብፁዕነታቸው €œይህ በአጠቃላይ የለየለት ጭካኔ ነው፤ ታይቶ የማይታወቅም ነው፡፡ ደግመን እንላለን እነዚህ ንጹሕ ክርስቲያኖች የተሰዉት የሃይማኖታቸውን ዓላማ ለማሳካት ነው፡፡ የግብጽና የኢትዮጵያዊያ ክርስቲያኖች መሠረታቸው አንድ ነው፤ ለዘመናትም የቆየ ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ክርስትና ቤተሰብ የሆኑትም በተመሳሳይ መገለጥና እውነታ ነው፤ ምንጫቸውም አንድ ነው፡፡ አሁንም በተመሳሳይ ሁኔታ ደማቸውን በሜድትራንያ ባሕር አፍስሰው ሰማዕት በመሆን የነበራቸው የተጋድሎ ምስክርነታቸው ተካፋይ ሆኑ€ በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡