Saturday, March 7, 2015

፬ተኛ ሳምንት መጻጕዕ




መጻጕዕ ማለት ድውይ በሽተኛ  ማለት ነው፡፡ ሳምንቱ በዚህ የተሰየመበት ዋናው ምክንያት በ ዮሐ 5÷1-9 እንደተፃፈው ለሠላሣ ስምንት ዓመታት በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ ይኖር የነበረ በሽተኛን ጌታችን አምላካችን መድሐኒታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ በተአምር የፈወሰበት  ሰንበት መታሰቢያ ስለሆነ ነው፡፡ይህ ድውይ የፀናበት ሰው በእብራይስጥ ቤተሳይዳ ወደምትባል መጠመቂያ ቦታ የሚወስደው ወገንና ዘመድ አጥቶ በመጠመቂያ አካባቢ   ለ38 ዓመት በአልጋው ላይ እንደተኛ ቆይቷል፡፡ ማዳን የባሕሪው የሆነው ጌታችን አምላካችን መድሐኒታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በአንድ ቃል  “ተነስና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” ብሎ ፈውሶታል፡፡ ነገር ግን “ተነስና ሂድ” ከማለቱ በፊት “መዳን ትወዳለህን?” ብሎ መልካም ምኞቱን ጠይቆታል፡፡ ለምን? መዳን ወዳለሁ ብሎ እንደሚመልስለት ያውቅ የለምን ስለምን እንዲህ ብሎ ጠየቀው? ይህም አላዋቂ የነበረን ስጋ እንደ ተዋሐደ ለማጠየቅ  እንዲህ ሲል ጠይቆታል፡፡ ድውዩም መዳን እወድ ነበር ነገር ግን ወደጸበሉ ተሸክሞ የሚያደርሰኝ የለም በማለት ብቸኝነቱን ተናግሯል፡፡ አባባሉም ጌታችን አምላካችን መድሐኒታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ በወቅቱ የሠላሣ ዓመት ወጣት ስለነበረ ተሸክሞ ወደ ጠበሉ ያደርሰኛል አልያም ብዙ ተከታዮች ስለነበሩት አንዱን ያዝልኛል ብሎ በማሰብ ነው፡፡ምክንያቱም አምላክነቱን ፣ ሁሉን ቻይነቱን አያውቅም ነበርና፡፡

ርዕትዕት ሃይማኖቶሙ ለቅዱሳን አበዊነ


በሰው ቂም አትያዝ በሰው ላይ ያለውን ቂም በልቦናው የሚያሳድር ሰው ጸሎቱ
ቅድመ እግዚአብሔር አትደርስምና ከአርዮሳውያን ጋር አትጸልይ እሊህም መናፍቃን ናቸው፡፡ ከአህዛብም ጋር ቢሆን፡፡(መዝ 4÷4-36(37) ፣ ማቴ 5 ÷ 5-14 ፣ ሮሜ 4 ÷ 4-19-2)


አንተ ሰውነትህን ለማድከም በምትጾምባቸው ዕለታት ወንድምህ ሊጠይቅህ ቢመጣ
እግዚአብሔርን ደስ በምታሰኝ በበጎ ሕሊና በፍቅር ሆነህ ከእርሱ ጋር ተመገብ ይህንንም የምነግርህ  የጌታ ጾም በሆነበት ዕለታት ትበላ ዘንድ አይደለም፡፡ እሊህም ረቡዕ እና
አርብ  አርባውም (ዓብይ ጾም) ቀን ናቸው፡፡ አንተ ብቻ በራስህ ፈቃድ
በምትጾምበት ቀን ነው እንጂ ይኸውም  ሰኞ ማክሰኞ ሐሙስ ነው፡፡
(ዳን 10 ÷ 2-3፣ማቴ 6÷16-18)

በቅዳሜ ቀን ግን መጾም አይገባም ፡፡በቅዳሜ ቀን ፀሐይ እስኪጠልቅ  መጾም የሚገባ ስራ አይደለም፡፡ እሁድ ግን በጠዋት  እጅግ ማልደህ ወደ ቤተክርስቲያን ሂድ ስትሄድም ልቦናህን በማባከን ወዲያ

Friday, March 6, 2015

ልብ ብለው ያንብቡት!

             
ከእለታት ባንድቀን አባት የሚጠባ ልጁን እንዲጠብቅለት ከውሻው ጋር ትቶት ወደ አደን ይሄዳ።  ከአደን ሲመለስ ውሻውን በደም ተጨማልቆ በሩ ላይ አገኘው። ውሻው የተጨማለቀበትን ደም ሲመለከት ልጁን በልቶት እንደሆነ ገመተ። ልክ ሁላችንም እንደምንገምተው በጣም ተናዶ ለአደን ይዞት የነበረውን መሳሪያ አቀባበለና ውሻውን የጥይት ሩምታ አወረደበት።የተረፉ የልጁን አካል ለማየት ወደ ውስጥ እየሮጠ ገባ። ነገር ግን ልጁ አንዳችም መጥፎ ነገርአላገኘውም። ይልቁንስ ከፊትለፊት በደም የተጨማለቀ ተኩላ ሞቶ ተመለከተ።ተመልከቱ ስሜቱ ሸፍኖት የዕድሜ ልክ ፀፀት የሆነበት ስራ ፈፀመ!!!። ስንቶቻችን ነገሮችን ሳናረጋግጥ ከብዙዎች
ተቆራርጠናል?  ልልህ የፈለኩት አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ፊትለፊት በምታይበት አይንህ ብቻ አትፍረድ! አዕምሮህንም ለፍርዱ ሹመት ስጠው! በችኮላ ስህተትን ሰርተህ ህይወትህን በሙሉ የሚፀፅትህ ነገር ውስጥ እንዳትገባ ተጠንቀቅ!!!።

Wednesday, March 4, 2015

ዜና;-የቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ሲመት 2ኛ ዓመት ተከበረ





 001abune matyas 1የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 2ኛ ዓመት የፕትርክና በዓለ ሲመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የካቲት 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ተከበረ፡፡

ቅዱስነታቸው በበዓሉ ላይ በሰጡት ቃለ ምእዳን “የእግዚአብሔር መንግሥት ማእከል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ጌታችን በሐዋርያት እንድትጠበቅ አድርጓል፡፡ ሐዋርያትም በበኩላቸው በተኳቸው ጳጳሳት እና ቀሳውስት ጠባቂነት ቤተ ክርስቲያን እንድትመራና እንድትጠበቅ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት፤ አንዲትና ቅድስት እንደመሆኗ መጠን ከመጀመሪያው አንስቶ መንፈሳዊውን ጥበቃ በጳጳሳትና በቀሳውስት ስታከናውን ኖራለች፡፡ አሁንም እያከናወነች ነው፤ ወደፊትም በዚሁ ትቀጥላለች” ብለዋል፡፡

ቅዱስነታቸው አያይዘውም ጳጳሳትና ቀሳውስት የተሰጣቸውን የጠባቂነት ሚና አስመልክቶም “ይሁንና በዘመናችን እየተነሳ ያለው መሠረታዊ ጥያቄ የእግዚአብሔር መንግሥት ተጠሪ የሆኑት ጠባቂዎች ሓላፊነታቸውን በሚፈለገው ሁኔታ እየተወጡ ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ በአሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፋዊና የወቅቱ ጥያቄ ሆኖ ይገኛል፡፡ የእግዚአብሔር መንጋ የሆኑት ክርስቲያኖችን በባሕር ማእበል ሞገድ እንደሚናጥ መርከብ በጥርጣሬ እየተናጡ አጉል መንገድ ላይ እንዲቀሩ እያደረገ ነው፡፡ ከመንጋው ተነጥሎ እንደሚቅበዘበዝ በግ ባለማመን ማእበል እያንጓለሉት ነው፡፡ በጠባቂነት

ዜና:- በዝቋላ ገዳም ዳግም የእሳት ቃጠሎ ተቀሰቀሰ





abune gebre menfes kidus 01 










በደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም በዛሬው እለት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ በምሥራቅ አቅጣጫ በሚገኘው ደን ዳግም የእሳት ቃጠሎ መቀስቀሱ ከገዳሙ አባቶች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በትናንትናው እለት ተቀስቅሶ የነበረው እሳት ከፍተኛ ርብርብ ተደርጎ ጠፍቶ የነበረ ቢሆንም በዛሬው እለት ተቀሰቀሰውን እሳት ለማጥፋት በገዳማውያኑ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ሰዓት እሳቱ ደኑን እያወደመ በከፍተኛ ሁኔታ እየተቀጣጠለ እንደሚገኝ የገለጹት ገዳማውያኑ ከደብረ ዘይት አየር ኃይል ሄሊኮፕተር እንዲላክላቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡