Friday, December 16, 2016



የገና ዛፍ
የገና ዛፍ ከየት መጣ ከእፅዋት ሁሉ የጽድ ዛፍ ብቻስ
ለምን ሆነ ?
የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርሰረቶስ
የልደት በዓል ሲከበር ዘውትር እያየናቸው ካሉና የበዓሉ አንድ
አካል እየሆኑ ከመጡ ነገሮች መሀከል ዋነኛው የገና ዛፍ ነው።
ይህን የገና ዛፍ አብዛኞቻችን ዝም ብለን ከማድረግ ባለፈ መቼቱ
የት እንደሆነ ምን አይነት ምስጢር እንዳለው የምናውቅ
አይመስለኝም ነገር ግን የቤተክርስቲያን ታሪክ ወደኋላ መለስ
ብለን ስናይ ምንጩ ከወዴት እንደሆነ ይነግረናል የመጀመሪያዎቹ
ክርስቲያኖችና ሐዋርያት በነበሩበት ዘመን ራሳቸውን የእውቀት
ባለቤት አድርገው የሚቆጥሩ በክርስትና ላይ የመጀመሪያውን
የምንፍቅና ትምህርት ማንሳት የጀመሩ  ግኖስቲክስ የሚባሉ
ሃሳውያን ነበሩ የስማቸው ትርጉም በግሪክ ቋንቋ ጠቢባን
አዋቂወች ማለት ነው። መሪያቸው ስምኦን መሰሪ ይባላል ይህ
ሰው በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሐዋርያትን የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ
በገንዘብ እንዲሸጡለት ጠይቋቸው የነበረ ደፋር ሰው ነው።
ታዲያ እነዚህ እርሱ የሚመራቸው እራሳቸውን ጥበበኞች ብለው
የሚጠሩ መናፍቃን ከፍልስፍና ሃይማኖታቸው ብዙ
አስተምህሮዎች መካከል ዋነኛው ሁለት አምላኮች አሉ
ብለው የሚያምኑት ነገር ሲሆን እነዚህ አማልክት አንዱ ክፉ
አንደኛው ደግሞ ደግ ናቸው ይላሉ።መልካም የሆኑና ጥሩ ናቸው

ብለው የሚያስቧቸውን ነገሮችን ሁሉ ለምሳሌ ከሰው ወንድን፣
ከወቅት በጋን ፣ፀሀይን፣ነፍስን፣ሰማይን፣ገነትን.....ደጉ አምላክ
ፈጠራቸው ፤ክፉው አምላክ ደግሞ የላይኞቹን ተቃራኒ የሆኑትን
ክረምትን፣ሴትን፣ስጋን፣ምድርን፣ሲኦልንና በአጠቃላይ መጥፎ
ናቸው ብለው የሚያስቧቸውን ሁሉ ፈጠረ ይላሉ። በዚህም
አስተምህሯቸው መሰረት በጋን የፈጠረው ደጉ አምላክ ከባዱን
የክረምት ወቅት የዝናቡን ጊዜ የሚያሳልፈው በጽድ ዛፋ ላይ
አድሮ ነው ብለው ያምናሉ። ለዚህ ደግሞ ማስረጃ የሚያረጉት
ጽድ በክረምትም በበጋም ወቅት ያለመድረቁ ምስጢርና
ቅጠሉም የማይረግፈው ለዛ ነው ብለው ያስቀምጣሉ።ይህ
ፍልስፍናቸውን ይዘውም ክረምታቸው በሚገባበት ጊዜ የጽድ ዛፍ
ላይ የተለያዩ ጌጣጌጦችን አድርጎ በማስዋብ ለደጉ አምላካቸው
አምልኮን ያቀርባሉ።ከጊዜ በኋላ ይህ የግኖስቲኮች የአምልኮ
ሥርዓት ልማድ ሆኖ ምዕራባውያንና አውሮፓውያን የጌታን ልደት
(
የዘመን መለወጫቸውን) በዓል ከማክበራቸው ከሳምንት በፊት
ጀምረው የጽድ ዛፍን በማሰጌጥ መብራቶችን በማንጠልጠል
ከበፊቱ በበለጠ ሥርዓቱን ይፈፅሙታል። የገና ዛፍ እና
ከእፅዋትም ጽድ የመሆኑ ነገር ታሪካዊ አመጣጡ ይህን
ይመስላል።
ወደ ሀገራችን ስንመጣ ደግሞ በእውቀት ማነስ ምክንያት በፊት
ዛፍ እየተቆረጠ አሁን ተመስሎ በተሰራው የፕላስቲክ ዛፍ
ኦርቶዶክሳዊ ምስጢር ኢትዮጵያዊ ባህልና ትውፊት የሌለውን
ይህን የመናፍቅ ሥርዓት ስንፈፅመው ኖረናል። ቤተ
ክርስቲያናችን ጌታችን በበረት እንደተወለደ በግርግም እንደተኛ
በጨርቅ ተጠቅልሎ ከከብቶች ትንፋሽ ሙቀትን እንዳገኘ ቦታው
በብርኃን ተሞልቶ መላዕክት ከሰወች ጋር በእንድነት እንደዘመሩ
እንጂ የጽድ ዛፍ በአካባቢው እንደነበር በዛስርም የሆነ ታሪክ
እንደተፈፀመ አታስተምርም። እርግጥነው የገና ዛፍ ቤት
ሊያደምቅ ሲያዩትም ሊያምር ይችላል ነገር ግን የጌታን ልደት
የሚያወሳ አንዳች ነገር አናገኝበትም ይልቅ ሳናውቀው
የግኖስቲኮችን የቆየ ምንፍቅና ቀጣይነት እንዲኖረው እንዳይጠፋ
እናደርጋለን እንጂ ።ስለዚህ ማንኛወንም ነገር ስናደርግ ለምን
እንደሆነ ምክንያቱን ቅድሚያ ማወቅ እንዳለብን ከዚህ እንረዳለን
ለምን ቢሉ አለማወቅ ከተጠያቂነት ስለማያድን በዘልማድ የሌላ
እምነት ሥርዓት ስንፈፅም ቆይተን በኋላ ስንጠየቅ እንዳናፍር
ነው።ስለሆነም በጌታችን ልደት ቀን ይህን ከማድረግ ተቆጥበን
ምስጢር ያለውና ሃይማኖታዊ ይዘቱን ሳይለቅ ባገኘናት ነገር
የበረት ግርግም ሰርተን የስነ ልደቱን ስዕል በመሀከል
በማስቀመጥ የሚበራውን ማድመቂያ በመለኮታዊው ብርሃን
መስለን ባማረ መልኩ የራሳችን የሆነ ትርጉም ያለው ልዩ ነገር
አዘጋጅተን ብርሃነ ልደቱን እያሰብን ማክበር እንችላለን

አምላካችን መዋዕለ ጾሙን በሰላም አስፈጽሞ ለብርሃነ ልደቱ
በጤና ያድርሰን።

No comments:

Post a Comment