የሄሮድስ ሰይፍ ቀልቷቸው
በስቃይ አልፋ ነፍሳቸው
በግፍ ያለቁ ሕፃናቱ
በአዳራሾችሽ ሲደሰቱ
በአማረው አክናፍ በረው በረው
ያለማቋረጥ አመስግነው
የእኒያ መላእክት ጥዑም ዜማ
እንዴት ይማረክ ሲሰማ
በአላውያን የግፍ ስለት
ከምድር ያለፉ ሰማዕታት
አክሊሉን ደፍተው በራሳቸው
በአምላክ ታብሶ እንባቸው
ለዓለም ዓለም ሲያርፉ
ከጠላት ወጥመድ ሲተርፉ
No comments:
Post a Comment