Saturday, April 4, 2015

፰ተኛ ሳምንት ሆሳዕና በቅዳሴ ጊዜ የሚደረግ ሥርዓተ አምልኮ





በዋናው ዲያቆን                  ዕብ    9 ÷11  
በረዳቱ ዲያቆን                   1ጴጥ   4÷1-12
በረዳቱ ቄስ                       የሐዋ   28÷11-22
ምስባክ፡-


እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ፤
በእንተ ጸላኢ፤
ከመትንስቶ ለጸላኢ ወለገፋኢ፡፡    መዝ 8 ÷2


ትርጉም፡-                               
ከሕፃናት አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህ፤
ስለጠላት ብለህ፤
ጠላትና ቂመኛን ታጠፋ ዘንድ፡፡


ወንጌል፡-                    ዮሐ   5 ÷ 11-13
ቅዳሴ፡-                     ዘጎርጎርዮስ

ሰሙነ ሕማማት



        የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊና ቱፊታዊ ክንዋኔዎች

በዐቢይ ጾም ከሰርክ ሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከነዚህ ክንዋኖዎች ውስጥ አለመሳሳም፣ አክፍሎት፣ ቄጤማ ማሰር፣ ጥብጠባ፣ ጉልባን እና ሕፅበተ እግር ይገኙበታል፡፡ ስለእነዚህ ክንዋኔዎች በቅድስት ቤተ ክስቲያን ስላለው ትውፊታዊ አፈፃፀም መዛግብት አገላብጠን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡
አለመሳሳም፡- በሰሙነ ሕማማት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምን የትክሻ ሰላምታ መለዋወጥን አይፈጽሙም፡፡ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማግሰኞ መከሩ አልሰመረላቸውም፡፡ ምክረቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡ ስለዚህ አይሁድ እያንሾካሾኩ እንሰቀለው ፤እንግለው ብለው ይማከሩ ነበር፡፡ በዘመነ ፍዳ ወቅት ሠላምና ፍቅር አለመኖሩን የሚገልፅልን በመሆኑ ያንን ለማስታወስ ስላምታ አንለዋወጥም፡፡ መስቀልም አንሳለምም፡፡ ሳምንቱ የክፋት ምክር የተመከረበት እንጂ የፍቅርና የደስታ ሳምንት የታየበት ባለመሆኑ ይህንን በማሰብ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ አይሁዳ ጌታን በጠላቶቹ ለማስያዝ እኔ የምስመው እርሱ ነው ያዙት ብሎ በሰላምታው ምልክት ሰጣቸው ይህ ሰላምታ አምሐ ቅድሳት አይደለም ተንኮል የተሞለበት እንጂ፡፡ የዲያቢሎስም ሰላምታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሔዋንን ስላም ለኪ ብሎ ነው ያታለላት የይሁዳም ሰላምታ ሰይጣናዊ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ወቅትና ሁኔታ ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ሰለምታ ልውውጥ የለም፡፡ ዛሬ እየተስተዋለ ያለው ይኽው ሰላምታ ያለመለዋወጥ ሁኔታ ስርወ መሰረቱ ይህ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እዚህ ትውልድ ላይ ደርሷል፡፡ ይቀጥላልም፡፡

እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም አደረሳችሁ!!





የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩስአሌም ሲገባ የሚቀድሙት እና የሚከተሉት ህዝብ በተለይም አእሩግ እና ህጻናትሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም ሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና በአርያምበማለት ጌታችንን መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው።
ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።

Wednesday, April 1, 2015

ዚቅ ወመዝሙር ዘሆሣዕና


ነግስ
ሰላም እብል ለዘዚአክሙ ቆም፡፡
ዓለማተ ዓለም ሥላሴ ዘአልብክሙ ዓለም፡፡
እምኔክሙ አሐዱ በእንተ ፩ዱ አዳም፡፡
እመኒ በምድር ተወክፎ ለነግደ ጲላጦስ ሕማም፡፡
ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም፡፡


ዚቅ
እም ሆሣዕናሁ አርአየ ተአምረ ወመንክረ፤
ዘኢተገብረ እምቅድመዝ፤
ወኢይከውን እምድኅረዝ፤



መልክአ ኢየሱስ ለዝክረ ስምከዚቅ
ሆሣዕና በአርያም ለወልደ ዳዊት ለንጉሠ እስራኤል፤
ዘይሁብ ዝናመ ተወን ከመ ትካት ይመልዕ ዓውደ እክል፤
በረከተ ምክያዳተ ወይን






ለመትከፍትከዚቅ
ኢይብክያ ዘከልዓ ደናግለ፤
አርዑተ መስቀል ፆረ፤
እስከ ቀራንዮስ ሖረ፤
ኢይብክያ ዘከልዓ ደናግለ፤

ለአእጋሪከዚቅ
ኦ አእጋር እለ አንሶሰዋ ውስተ ገነት፤
ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል

መዝሙር
ሃሌ ሉያ፣ ሃሌ ሉያ፣ ሃሌ ሉያ፣
ሃሌ ሉያ፣ ሃሌ ሉያ
ወእነዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ፤
ኀበ ደብረዘይት ሙራደ ዐቀብ ሀገረ እግዚአብሔር፤
ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት፤
ነሲኦሙ አእፁቀ በቀልት፤
እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም፤
ተጽኢኖ ዲበ እዋል ቦኣ ሀገረ ኢየሩሳሌም፤
በትፍሥሕት ወበሐሤት ይሁቦሙ ኃይለ ወስልጣነ፤

ምልጣን
እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም፤
ተጽኢኖ ዲበ እዋል ቦኣ ሀገረ ኢየሩሳሌም ፤
በትፍሥሕት ወበሐሤት ይሁቦሙ ኃይለ ወስልጣነ፤





ወስብሐት ለእግዚአብሔር