እንኳን ለዘመነ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ፡፡ በቤተክርስቲያናችን ዘመነ ጽጌን እና የእመቤታችንን ስደት አስመልክቶ ለሚቀጥሉት 6 እሑዶች (መስከረም ፴ ጥቅምት፯ ጥቅምት፲፬ ጥቅምት፳፩ ጥቅምት፳፰ ኅዳር፭) የሚቆመውን የማኅሌተ ጽጌ ዚቅና መዝሙር በየሳምንቱ ይዘንላችሁ እንቀርባለን::
ነግሥ ለኵልያቲክሙ...ዚቅ
ወኃይዝተ ወንጌል የዓውዳ ለቤተክርስቲያን፤
እም አርባዕቱ አፍላጋት፤
እንተ ትሰቀይ ትእምርተ ለለጽባሑ፤
እማቴዎስ ልደቶ ወእማርቆስ መንክራቶ፤
እም ሉቃስ ዜናዊ ተሰምዮ ወእም ዮሐንስ በግዓ፤
ወዘንተ ሰሚዓ ትገብር በዓለ በፍግዓ፤
ማኅሌተ ጽጌ
ጽጌ አስተርአየ ሠሪፆ እምዐፅሙ፤
ለዘአማኃኪ ጽጌ ለገብርኤል በይነ ሰላሙ፤
ወበእንተዝ ማርያም ሶበ ሐወዘኒ መዓዛ ጣዕሙ፤
ለተአምርኪ አኀሊ እሙ ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ፤
ድሚያ ከዘመን ወደ ዘመን ያሸጋገረን ለብርሃነ መስቀሉ ያደረሰን በሀብቱ የሳበን በረድኤቱም ያቀረበን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡







አሸባሪው አይ ኤስ አይ ኤስ 30 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን መግደሉንና ለዚህም ሓላፊነቱን መውሰዱን ተናግሯል፡፡ ክርስቲያኖቹን በመግደሉ ይቅር እንለዋለን፤ እንጸልይለታለንም፡፡ በማለት ብፁዕ አቡነ አንጄሎስ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላላፈዋል፡፡


